Get Mystery Box with random crypto!

#የድረገጽ_ጥቆማ በነፃ የቢዝነስ ኮርሶችን መውሰድ ትፈልጋላችሁ አዎ ከሆነ መልሳችሁ፤ እንደሚከ | Ethiopia

#የድረገጽ_ጥቆማ

በነፃ የቢዝነስ ኮርሶችን መውሰድ ትፈልጋላችሁ

አዎ ከሆነ መልሳችሁ፤ እንደሚከተለው ይቀርባል...

ዛሬ የምናስተዋውቃችሁ ድረገጽ፤ በነፃ የቢዝነስ ኮርሶች የምታገኙበትን ነው፡፡ አለም አቀፍ የንግድ ሴንተር (International Trade Centre)፤ በንግድ ስራ ዙሪያ የተለያዩ ኮርሶችን በኢንተርኔት በነፃ ይሰጣል፡፡ ድርጅቱ አነስተኛ እና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶችን ለመደገፍ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ ኮርሶችም የሚያተኩሩት:-

- በኤክስፖርት ቢዝነስ ላይ

- በስራ ፈጠራ (ኢንተርፕረነርሺፕ) ላይ

- ዲጂታል ማርኬቲንግ እና የመሳሰሉት ከንግድ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡

ኮርሶቹ በአብዛኛው ከሁለት እሰከ አራት ሳምንት (በሳምንት 2 ሰአታት) የሚወስዱ ናቸው።

ለመመዝገብም የሚያስፈልግን የራሳችን የኢ-ሜል አድራሻ ሲሆን ትምህርቱም ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት የሚሰጥ ነው፡፡

በዚህ ድረገጽ ላይ የሚገኙ ኮርሶች አብዛኛዎቹ ለንግድ ስራ የሚሆኑ ስለሆነ የራሳችንን ቢዝነስ ለመክፈት የምንፈልግ ከሆነ፣ የቢዝነስ ድርጅቶች ውስጥ የምንሰራ ወይም የቢዝነስ ትምህርት የምንማር ከሆነ በጣም ጠቃሚ ናቸው፡፡

ድረገጽ ላይ የሚሰጡትን ኮርሶች ለመውሰድ የሚያስፈልገን ነገሮች:-

1. ድረገጹ ላይ ለመመዝገብ የራሳችን የኢሜል አድራሻ ማዘጋጀት እና

2. ከተመዘገብን በኋላ የምንፈልገውን ኮርስ ከድረገጹ ላይ መርጠን፤ መመዝገብ እና መማር፡፡

ኮርሶቹን በራሳችን ፍጥነት እዛው ኢንተርኔት ላይ ማንበብ እና መማር እንችላለን፡፡ ኮርሱን ከጨረስን በኋላ መማራችንን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ከድረገጹ ላይ ማውረድ እንችላለን። ከታች ሊንኩን በመንካት ድረገጹን ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡

https://learning.intracen.org

ምንጭ:- Wede Sera ወደ ስራ


Join for more

@info_tech1
@info_tech1