Get Mystery Box with random crypto!

ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው...(1ኛ ዮሐ.3፡15) “ብሔርተኛ የሆነ አምባገነናዊ አገ | የስብዕና ልህቀት

ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው...(1ኛ ዮሐ.3፡15)

“ብሔርተኛ የሆነ አምባገነናዊ አገዛዝ ለጊዜው ምክንያታዊነት በጎደለው ስሜታዊና ግልብ በሆነ አስተሳሰብ ዜጋውን ወይም “ብሔር” ብሎ ከፋፍሎ ያደራጃቸውን በመንዳት የተሳካለት ይምሰለው እንጂ፣ አገዛዙን ለማስቀጠል ሲል የሚፈጽማቸውን ግፎች በሂደት ሕዝቡ እየተገነዘበው ስለሚሄድ ምንም ዓይነት ሴራ ቢጠቀም አገዛዙ ያሰበው እቅድ ዘለቄታ ሊኖረው አይችልም፡፡

በአንድ ሀገር ውስጥ ብዙሃን ይሁን አናሳ ቁጥር ባለው “በብሔር” ማንነት
ላይ የተመሠረተ ማንኛውም አገዛዝ የሳይንሳዊ ፖለቲካዊ ስርአት ሳይሆን በአዕምሮ ቅዠት ህመም የተጠቃ፣ ፋሽስታዊ አምባገነን፣ ኢ-ሰብአዊ፣ ስርአተ አልበኛ፣ የወሮበላና የደንቆሮ ገዢ ቡድን ነው፡፡ በአጠቃላይ “የብሔርተኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ በፖለቲካ ሳይንስ የተቃኘ ሕዝባዊ አስተዳደር ሳይሆን፣ ከአዕምሮ ቅዠት ህመም የመነጨ የድንቁርና አገዛዝ ነው::

በአሁኑ ዓለም የመልካም አስተዳደር ሳይንሳዊ ፖለቲካ ማለት፣ የአንድ ሀገርን ብዙሃን ሕዝብ አዕምሮ ከፖለቲካዊ ቁጭት፣ ጥላቻና በቀል ነጻ በማድረግ በኑሮ ደረጃዉ እያሳደገ የማስቀጠል ብቃት ነው፡፡


በአንድ ሀገር መንግሥታዊ አገዛዝ ላይ ብዙሃኑ ሕዝብ አዕምሮ ውስጥ ቁጭት፣ ጥላቻና በቀል ከተፈጠረ ሀገሪቱ የብዙሃን ሕዝብ ድጋፍ የተቸረው የአገዛዝ ሥርዓት ባለመሆኑ ሀገሪቱ ያልተረጋጋችና ልማቷም ዘለቄታ የሌለዉ ስለመሆኑ ማሳያ ነው፡፡ ይህም ቁጭት፣ ንዴትና ጥላቻ እያደገ በመሄድ በዋናነት በአፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያን የመሳሰሉትን ሀገራት ሁልጊዜ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እየከተተ ዜጋውን ወደተሻለ ኑሮ እንዳያድግ የሚገድብ ነው፡፡

ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው...(ኛዮሐ.3፡15)፡፡ አንድ ሰው ግድያ ከመፈጸሙ በፊት የሚፈጠረው የጥላቻ አስተሳሰብ ይቀድማል፡፡ የጥላቻውም አስተሳሰብ በሂደት በግድያ ድርጊት ይፈጸማል፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥ ብዙሃኑ ሕዝብ በፊት ስለሚገድለው ሰው በአዕምሮው ውስጥ  ቁጭት፣ ንዴትና ጥላቻን የሚፈጥር መንግሥት ካለ አምባገነን አገዛዝ እንጂ፣ መንግሥታዊ ስርአት አይደለም፡፡ ስርአት ማለት ማንም ሰው እንደፈለገው የማይቀያይረው፣ በሳይንሳዊ እውቀት የተደራጀ፣ ህግንና ደንብን በመከተል የታለመለትን ግብ የያዘ ተቋም  ነው፡፡

“የብሔርተኛ” አምባገነናዊ አገዛዝ ሳይንሳዊ የፖለቲካ ስርአት ሳይሆን፣ በባህሪው በቀሪው ዜጋ አዕምሮ ውስጥ ሁልጊዜ ቁጭት፣ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ ንዴትና ጥላቻን የሚፈጥር የስርአተ አልበኛና የአሸባሪነት አገዛዝ ነው፡፡ የብዙሃኑ ህዘብ አዕምሮ ለቁጨት፣ ለንዴትና ለጥላቻ የሚዳርግ አገዛዝ ይዋል ይደር እንጂ፣ አንድ ቀን በብዙሃኑ ህዝብ አመጽ በውርደት መወገዱ እንደማይቀር የአሁኑ ዓለም ታሪካዊ ሃቅ ነው፡፡ በአሁኑ ዓለም “በብሔር” ማንነት ላይ የተመሠረተ ፋሽስታዊ አገዛዝ በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚዊ እንዲሁም በኃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ እንኳ ሳይቀር የበላይነቱን በማረጋገጥ ሰውን ከሰው የሚለይ፣ የሚያገልና አድልኦን የሚፈጽም ሳይንሳዊ ያልሆነ አገዛዝ ነው፡፡ ስለሆነም በብዙሃኑ ሕዝብ ዘንድ ምንጊዜም ቢሆን ተቀባይነት ስለሌለው ሁልጊዜ ሰላምና መረጋጋትን በማሳጣት ለአብዮት የሚዳርግ ነው፡፡

በ”ብሔር” ማንንነት አዕምሮ በተቃኘ ፋሺስታዊ አገዛዝ ውስጥ ሁሉም ባይቀበለውም ነገር ግን እጅግ አብዛኛው ዜጋ በ”ብሔር” ማንንነት አዕምሮ ቅዠት ህመም ይለከፋል፡፡ የ”ብሔርተኛ” ፋሽስታዊ አገዛዝ የስልጣኑን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲል የሚያራምዳቸው መሠረታዊ ሴራዎች አሉት፡፡ እነዚህ ሴራዎችም በህዝብ አዕምሮ ውስጥ ቁጭት፣ ንዴትንና ጥላቻን በአገዛዙ ላይ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመሩ ይሄዳሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ቁጭት፣ ጥላቻ ይዋል ይደር እንጂ “በብሔር” ማንነት ተከፋፍሎ የነበረውን ሕዝብ ወደ መተባበበር ይገፋፋውና አገዛዙን ለማስወገድ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ ሳይወድ በግዱ ይገባል፡፡

ሰብስቤ አለምነህ

@Zephilosophy
@Zephilosophy