Get Mystery Box with random crypto!

ብዙ ሰዎች ያለንበት አጠቃላይ አገራዊ ሁኔታ ያሳስባቸዋል። የኑሮ ውድነት ያስጨንቃቸዋል፥ ተደጋጋሚ | የስብዕና ልህቀት

ብዙ ሰዎች ያለንበት አጠቃላይ አገራዊ ሁኔታ ያሳስባቸዋል። የኑሮ ውድነት ያስጨንቃቸዋል፥ ተደጋጋሚ ግጭት ረፍት ይነሳቸዋል። ቢሆንም ምንም ማለት አይፈልጉም።

"እኔ ምንም ማምጣት አልችልም" ይላሉ። የዚህ ሰበቡ ሁለት ነው። ተስፋ መቁረጥ ወይንም ህዝባዊ አቅምን አለመገንዘብ!

በእርግጥ በተደጋጋሚ ድምፅ አሰምተን ጠብ ያለ ነገር አልታየን ይሆናል። እንደ ህዝብም መተባበር እንደማንችል ልናስብም እንችላለን።

እውነታው፥ ትንንሽ ነጠብጣቦች ተደማምረው ትልቁን ምስል ይፈጥሩታል። በግል የምንጠይቀው የመብት ጥያቄ አንዲት ነጥብ ናት። "ኑሮ ውድነቱ ይብቃ፥ ግጭት ይቁም፥ መብት ይከበር" ማለታችን አንዲት ትንሽ ነጥብ ናት። የእያንዳንዳችን ነጠብጣቦች ሲደመሩ ትልቁን ምስል ይሰራሉ!

አምባገነኖች አቅመ ቢስነት የሚሰማቸው ተስፋ ቢስ ዜጎችን ይፈልጋሉ። ደካማነት የሚሰማውን ህዝብ እንዳሻቸው ይነዱታልና!

አምባገነኖች እንዴት መተባበር እንዳለበት የማያውቅን ህዝብ ይመርጣሉ። የዜጎች አለመተባበር ለጭቆና ይረዳቸዋልና!

ተስፋ ቢሶች አንሁን፥ ጠጠር እናዋጣ። የእያንዳዳችን የመብት ጥያቄ እንደ ነጠላ ጡብ ተደማምሮ የነፃነትን ህንፃ ይገነባሉ።

'እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ' ከማለት ይልቅ 'መብቴ ይከበር' የማለትን ድፍረት እናዳብር !

ተስፋብዓብ ተሾመ
@Human_Intelligence
@Tfanos