Get Mystery Box with random crypto!

ሀገር ያጣ ሞት ሄኖክ በቀለ ነፃነት ሲፋለሙለት እንጂ ሲኖሩት እጅግም አይደላም። አንዳንዴ ታጋይ | የስብዕና ልህቀት

ሀገር ያጣ ሞት
ሄኖክ በቀለ

ነፃነት ሲፋለሙለት እንጂ ሲኖሩት እጅግም አይደላም። አንዳንዴ ታጋይ ሁሉ በደል አማርሮት ታግሎ ሲያበቃ፤ የታገለውን የሚያስከነዳ በዳይ ይሆናል። በተመደበለት ሚዛን አትረፍርፎ ይሰፍራል። ሚስቱ የኮበለለችበት የእገሌን ሚስት ያስኮበልላል። ሲኮረኩሙት ያደገ ልጅ፤ ልጅ የወለደ ቀን በኩርኩም እየቀመቀመ ይገድለዋል። በጅራፍ የተገረፈ በጊንጥ ይገርፋል።አልቃሽ ሁሉ ቀንና ዕድል ያልገጠሙለት አስለቃሽ ነው። ልብ ብለን ካስተዋልነው ከእግረ ሙቁ የተላቀቀ፤ ሰንሰለቱን የበጠሰን ሁሉ “ነጻ ወጥቷል” ማለት አይቻልም። ባርነቱን ድቡልቡል አንጎሉ ውስጥ ሸሽጎ መቀለቡን አይተውም። የቀለቡት ደግሞ መፋፋቱ መች ይቀራል?

በዳይ ግን ቀድሞ ሁሉን አይቷልና ውለታ እያደረገ እንደሆነ ያስባል። ታጋይን ሸምቅቆ ከነጻነቱ ይከላከለዋል። ሕይወት ይኸው አይደል? ከአንድ አምባገነን ወደ ሌላ አምባገነን የሚደረግ ሶምሶማ፤ ጨቋኝ እስከሚሆኑ እየተጨቆኑ የሚኖሩት የደንገላሳ፤ መውጫ የሌለው፤ መድረሻና መነሻው የማይለይ የነሲብ ክብ ሽምጥ...

@Human_Intelligence