Get Mystery Box with random crypto!

በፌደራሊዝም ሰም የሚማማሉ ሰዎች ፌደራሊስት መሆን ሲሳናቸው ደጋግመን አይተናን ታዝበናል። ፀሐዩ | የስብዕና ልህቀት

በፌደራሊዝም ሰም የሚማማሉ ሰዎች ፌደራሊስት መሆን ሲሳናቸው ደጋግመን አይተናን ታዝበናል።

ፀሐዩ መንግስታችን "አሓዳዊነትን አስወግጄ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት አስከብሬያለሁ" ማለት ከጀመረ 30 አመት ተሻግሯል።

ሐቅ መናገር ካለብን፥ 'ራስን በራስ ማስተዳደር' የሚሉት ጨዋታ የፖለቲካ ሽንገላ ነው።

በየቀበሌው ያሉ ሹማምንት የቀበሌውን ነዋሪ የማያውቁ ናቸው። ለከተሞች መሪ የሚሆኑት የገጠር ካድሬዎች ናቸው። ወረዳዎችና ዞኖች የራሳቸውን መሪ አይመርጡም።

ዜጎች ፦ ለቀበሌያቸው ሊቀመንበር ካልመረጡ፥ ለከተማቸው አስተዳዳሪ ካልሾሙ፥ ለወራዳ እና ዞናቸው መሪ ካልሰየሙ .... ራስ ማስተዳደር የሚለው ተረት ሽንገላ ሆነ ማለት አይደለም?

"ራስን በራስ ማስተዳደር" ማለት በዜጎች ያልተመረጡ ነገር ግን የአከባቢውን ቋንቋ በሚናገሩ ሹማምንት መገዛት ማለት ነው?

ለአዳማ ከንቲባ ከአምቦ እየተላከ፥ ለባህር ዳር አስተዳዳሪ ከደምበጫ እየተመደበ ፥ ለመቀለ ደግሞ ከሽረ እየተወከለ ስለ ፌደራሊዝም ማውራት ውሸት አይሆንም?

ከማዕከል ገዢ መመደብ ኋላ ቀርነት እና አጭበርባሪነት ነው።

ዜጎች "መሪዎቻችንን የመምረጥ መብታችን ይከበር" የሚል ጥያቄ ማንሳት አለባቸው። ልከኛው ራስን የማስተዳደር መንገድ ይኸው ነው !


@Tfanos