Get Mystery Box with random crypto!

#Frog_Experiment ዒላማህን ምታ ______ ውሃ በተሞላ ድስት አንዲት እንቁራሪት ብን | የስብዕና ልህቀት

#Frog_Experiment

ዒላማህን ምታ
______
ውሃ በተሞላ ድስት አንዲት እንቁራሪት ብንጨምር እና ከዛም ውሃውን ማፍላት ብንጀምር ፤ ውሃው እየፈላ በሄደ ቁጥር እንቁራሪቷም የሰውነት ሙቀቷን ማስተካከል ትጀምራለች።

የውሃው ሙቀት ከፍተኛ እየሆነ ሲሄድ እሷም የሰውነቷን ሙቀት በዛው ልክ ማስተካከሉን ትቀጥላለች። የውሃው ሙቀት ጨምሮ የመፍላት ደረጃ (boiling point) ላይ ሲደርስ ግን ማስተካከል ማትችልበት ደረጃ ስለሚደርስ እራሷን ለማዳን ከድስቱ ዘላ ለመውጣት ትፈልጋለች ፤ ትሞክራለችም ፤ ግን ዘላ መውጣት አቅም አይኖራትም አትችልም። ምክንያቱም ያላትን አቅም ሁሉ ሙቀቷን በማስተካከል የውሃውን ቃጠሎ ለመከላከልና ለመላመድ ባደረገችው ተጋድሎ ጨርሳዋለችና ወድያው ትሞታለች፡፡

እንቁራሪቷን ምን ገደላት ???

አብዛኞቻቸችን የፈላ ውሃ እንል ይሆናል ፤ እውነታው ግን ይህ አይደለም። እንቁራሪቷን የገደላት የፈላው ውሃ ሳይሆን መች መዝለል እንዳለባት የመወሰን እቅም ማጣቷ ነው።

አብዛኞቻችን ከሰዎችም ይሁን ከነገሮች ጋር ያለንን ነገር ለማስተካከልና ለመላመድ እንሞክር ይሆናል፤ ግን እስከ መች ማስተካከል እንዳለብንና መች መወሰን እንዳለብን ማውቅ ይሳነናል።

አንዳንዴ ነገሮችን እንለምዳቸውና ለኛ የማይጎዱ መስለው ይታዩናል፤ በመጨረሻው ቅፅበት ግን እንዳለመድናቸው ቢገባንም ማመልጥና መውጣት የማይቻለን ሰአት ይሆናል።

በጥፋት/ወንጀል መንገድ ውሰጥም ስንሆን እንዲሁ ነው፤ ትንሹን ወንጀል እንለምደዋለን የሚጎዳን አይመስለንም፤ ደስታ ውስጥ ያለን ይመስለናል፤ ደስታው ሙቀት ይፈጥርልናል፡፡

ሙቀቱ ወደ እሳት የተቀየረ ጊዜ ግን ፍፃሜው ግልፅ ነው፡፡ ከሙቀቱ መውጣት ካልቻልን ከእሳት እንደማንወጣ ግልፅ ነው። እናም ለውሳኔ አንዘግይ !!!

ምንጭ | ከመጻሕፍት ዓለም ገጽ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence