Get Mystery Box with random crypto!

ልክ እንደ ወንዝ! “ወንዝ ሲፈስ አነስተኛ የመቋቋም ብቃት ወዳለው አቅጣጫ እየተጣጠፈ ነው የሚዘል | የስብዕና ልህቀት

ልክ እንደ ወንዝ!

“ወንዝ ሲፈስ አነስተኛ የመቋቋም ብቃት ወዳለው አቅጣጫ እየተጣጠፈ ነው የሚዘልቀው” ይባላል፡፡ አቅሙ የሚፈቅድለት ቁልቁለቱ እያለለት ወንዝ ከአቅሙ በላይ ወደሆነው ወደዳገቱ አይፈስም፡፡ እንደ አቅሙ የሆነው እያለለት ወንዝ ከአቅሙ በላይ የሆነውን፣ “ለምን አያሳልፈኝም” እያለ አይታገልም፡፡ አሁን ስለቀለለው ወደቀኝ ታጥፎ፣ ወዲያው ሲከብደው ወደግራ ሊታጠፍ ይችላል፡፡ በዚህ የፍሰት ባህሪይው የወንዝ መጨረሻው ቀጥ ብሎ ከመሄድ ይልቅ እየተጣመሙ መኖርና የአካባቢው ዝቅተኛው ስፍራ ላይ መውረድ ነው፡፡

የወንዝ ባህሪይ ግን ከላይ የተገለጸው ብቻ አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኮ ወንዝ ወደከፍታም የሚፈስበት ጊዜ አለ፡፡  ወንዝ አቅሙን ሲያጠራቅም፣ ሲበረታና ኃይል ሲኖረው በፊቱ ያለውን ከፍ ያለ ነገርም ቢሆን ሞልቶና አልፎ ይሄዳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወንዝ ሲበረታ ከፍተኛውን ስፍራ እስኪሞላ ድረስ “ወደ ላይ ይፈስሳል”፡፡

ከወንዝ እንማር! ከአቅምህ በላይ የሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙህ ለምን መንገድ አይለቁም ብለህ እስክትደማ አትታገል፣ ወይም ደግሞ ወደኋለ አትመለስ፡፡ ብልሃት ፈልገህ ዘወር ብለህ እለፍ፡፡ ሆኖም ያንን እያደረክ ሳለህ፣ አቅምህን አጠራቅም፡፡ አቅም በጨመርክ ቁጥር መንገድ እየቀየርክና ጠመዝማዛ ጎዳናን በመጓዝ መድከምህ ያበቃና ቀጥ ብለህና በፊትህ የሚቆመውን እየገረሰስክ ማለፍ ትጀምራለህ፡፡

•  የስሜት ጽንአት አቅምህን አጠራቅም፣ እስከዚያ ግን የወቅቱን የስሜት ጽንአት ባገናዘበ ሁኔታ ተራመድ፡፡

•  የገንዘብ አቅምህን አጠራቅም፣ ለጊዜው ግን ኑሮህን ካለህ የገንዘብ አቅም ጋር በማገናዝ ተንቀሳቀስ፡፡

•  የግንኙነት መረብህ (Network) አቅምህን አጠራቅም፣ እስከዚያው ግን አጠገብህ የሚገኙ ሰዎች በሚደግፉህ ደረጃ ተራመድ፡፡

•  የእውቀት አቅምህን አጠራቅም፣ እስከዚያው ግን ባለህ እውቀት የምትችለውን ስራ በመስራት ኑሮህን ግፋ፡፡

ልክ እንደወንዝ!!!

ዶ/ር እዮብ ማሞ


@Human_Intelligence
@Human_Intelligence