Get Mystery Box with random crypto!

የተካደ ትውልድ (በእውቀቱ ስዩም) የተካደ ትውልድ አይዞህ  ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠ | የስብዕና ልህቀት

የተካደ ትውልድ
(በእውቀቱ ስዩም)
የተካደ ትውልድ
አይዞህ  ባይ የሌለው
ታዳጊ የሌለው
ወይ ጠባቂ መላክ፥ ወይ አበጀ የሚለው
ደርሶ ከቀንበሩ ፥የማይገላግለው፤

የተካደ ትውልድ

አብዝቶ የጾመ፥ ተግቶ የጸለየ
ጥቂት መና ሳይሆን፥ ጥይት  ሲዘንብ ያየ
እድሜ ይፍታህ ተብሎ፥ የተወለደ ለት
አምባሩ ካቴና፥ ማተቡ ሰንሰለት፤

ምቾትን የማያውቅ፥ ረፍት የተቀማ
አልጋው ያጋም እሾህ፥ መኝታው የሳማ፤

የተካደ ትውልድ

ሞቶ እንኳን ሬሳው፥ አይላላለት ቀንበር
በዘብ እጅ ተገድሎ ፥ በሹም የሚቀበር
ከጡት አስጥል በላይ፥ ኑሮ የመረረው
እንዳይሄድ ጎዳናው ፥ የተደናገረው
ድል ያልሰመረለት ፥ትግል ሳይቸግረው።

የተካደ ትውልድ
በስጋ በነፍሱ
በቀልቡ በገላው
ከቶ ምንድን ይሆን?
ምንድን ይሆን መላው?

#በእውቀቱ_ስዩም

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence