Get Mystery Box with random crypto!

ድሆች ነን! በድህነት የተነሳ ብዙ ነገራችንን ያጣን አሳዛኝ ድሆች ነን። ለማጣታችን ብዙ ሰበብ መ | የስብዕና ልህቀት

ድሆች ነን! በድህነት የተነሳ ብዙ ነገራችንን ያጣን አሳዛኝ ድሆች ነን።

ለማጣታችን ብዙ ሰበብ መደርደር እንችላለን። አገዛዞቻችን ግን ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው። በዘመናት መሓከል ወደ መንበር የወጡ የኢትዮጵያ መሪዎች የሚያበጁት ስርኣት የንጥቂያ ነው። ዜጎች በጭካኔ እንዲበዘበዙ ሆነዋል።

በነገስታት ዘመን፥ ገበሬዎች ጭሰኛ ሆነው የድካማቸውን ውጤት መሳፍንቱ በልተዋል። አምራቾች በገዛ ሃገራቸው ባይተዋር ተደርገው ልፋታቸውን ሌሎች ጠግበውበታል። ገበሬው ገባር ነበር!

ደርግ ገበሬውን ከጭሰኝነት አላቅቄያለሁ ቢልም በተራው አስገባሪ ሆኗል። ሰዎች በገዛ ድካማቸው ያመረቱትን በነፃነት እንዳይሸምቱ ገደብን አበጅቷል። በሰበብ አስባብ የዜጎችን ሃብት ቀምቷል።

ኢህአዴግ እና ብልፅግና "ከቀደሙት እሻላለሁ" ቢሉም ነገራቸው ተመሳሳይ ነው። ሆነ ብለው ኢንፍሌሽን በመፍጠር ዜጎችን ይመዘብራሉ። የገንዘብን የመግዛት አቅም በማሽመድመድ የራሳቸውን ኔት ወርክ ያበለጥጋሉ።

በሐገራችን ወደ መንበር የሚወጡት ሁሉ ቀማኞች ናቸው።

ዜጎች በገዛ ንብረታቸው ላይ ነፃነት የላቸውም።

መንግስት ያስፈለገው ለዜጎች ዋስትና እንዲሰጥ ቢሆንም እኛ ለዚህ አልታደልንም።

ያለ ነፃነት ከድህነት መውጣት አይቻልም! "መብታችንን ስጡን፥ ዳቧችንን እኛው እንጋግራለን" ማለት መጀመር አለብን !


@Tfanos

@Human_Intelligence