Get Mystery Box with random crypto!

እንዴት ንጉስ መሆን ይቻላል-ማኪያቬሊ ወደ ላይ መውጣት ከፈለግክ የግድ የበታቾችህን መጨፍለቅ ይኖ | የስብዕና ልህቀት

እንዴት ንጉስ መሆን ይቻላል-ማኪያቬሊ

ወደ ላይ መውጣት ከፈለግክ የግድ የበታቾችህን መጨፍለቅ ይኖርብሃልን? ስኬት የሚመጣው ሰዎችን በማታለል እና በክፋት ውስጥ ብቻ ነውን?

ስለምንድን ነው በአብዛኛው ዘርፍ ላይ ከላይ የሚሆኑ ባለ ስልጣናት ወይም አለቆች የእብደት ጠባይ ያላቸው?
የዲፕሎማቱ እና ፈላስፋው ማኪያቬሊ መጽሐፍ የሆነው The Prince ለዚህ መልስ አለው። ይህ አጭር መጽሐፍ እንዴት ምርጥ እና ስኬታማ መሪ እንደምትሆን ያሳይሃል፡፡ ምርጥ መሪ ማለት መልካም መሪ የሚል ቀጥተኛ ትርጓሜ የለውም፡፡ ምርጥ መሪ በምንም አይነት መንገድ ስልጣኑን የሚያስጠብቅ መሪ ነው። ይህ መሪ ያጭበረብራል፣ ይሰርቃል፣ ህዝቡን ያታልላል ሆኖም በመጨረሻ የሀገሪቷን ሰላም እና ደህንነት በሚገባ ያስጠብቃል፡፡ የራሱን የስልጣን ዘመን ያራዝማል፡፡

በመጽሐፉ ውስጥ እነዚህን ምክሮች እናገኛቸዋለን፡፡
“በማታለል የምታገኘውን ነገር ኃይል በመጠቀም ለማሸነፍ አትሞክር”

“ፍቅር እና ፍርሃት በአንድ ሊኖሩ ስለማይችሉ... ከመወደድ ይልቅ መፈራትን ምረጥ”

“በንጉስህ ላይ ከተኮስክ ላለመሳትህ እርግጠኛ ሁን”

አሁን ላይ ማኪያቬሊ ይህን መጽሐፍ ባለ ስልጣኖች ላይ ለመሳለቅ የጻፈው ይሁን አልያም አቋራጭ የስልጣንን መንገድ ሊያሳየን፤ እርግጠኛ ሆነን መናገር አንችልም፡፡ ሆኖም የThe art of war ጸሐፊ - ሰን ዘ'ም ሆነ ማኪያቬሊ ስልጣን - በጭካኔ፣ በኃይል እና በማታለል እንደሚገኝ አሳይተውናል።

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence