Get Mystery Box with random crypto!

እረፉ!!!! “ዘመመ!” ብላችሁ የሰው ቤት አትግፉ እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ። እረፍ!!!! | የስብዕና ልህቀት

እረፉ!!!!
“ዘመመ!” ብላችሁ የሰው ቤት አትግፉ
እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ።

እረፍ!!!!
“ቆሜያለሁ!” ለማለት አጥሬን አትደገፍ
ለአመዳም ወዘናህ ቆዳዬን አትግፈፍ።

እረፍ!!!!
በመስመርህ ፍካ በድንበርህ ለምልም
በየአልጋህ እደር በየእንቅልፍህ አልም።

እረፊ!!!
በኩረጃ ንባብ ትርጉም አትግደፊ
በሰባራ መርፌሽ የሰው ልክ አትስፊ።


ማን አንደጠለፈኝ ማን እንደሰበረኝ
ጠያቂ አጣሁ እንጂ መልስማ ነበረኝ።
ምክንያት ታመመ መፍትሄ ታመመ
ከጥያቄው በፊት መልሱ እየቀደመ።

ሌብነት ገነነ
ግርግር ገነነ
ብልጭልጭ ገነነ
ድንግርግር ገነነ
ኪሳራ ገነነ
ደላሎች ገነኑ፣ ደላሎች ጀገኑ
ባልዋለ ገበያ ዋጋ እየተመኑ!!!!!

ምክንያት ታመመ መፍትሔ ታመመ
ከጥያቄ በፊት መልስ እየቀደመ ::

እያዩ ፈንገስ
በረከት በላይነህ

@Human_Intelligence