Get Mystery Box with random crypto!

#ለጨረቃዋ_አልም!!! ለጊዜው የማይደረስባቸው ቢመስሉህ እንኳ የሚያነሳሱህን ግቦች አስቀምጥ፡፡ በ | የስብዕና ልህቀት

#ለጨረቃዋ_አልም!!!

ለጊዜው የማይደረስባቸው ቢመስሉህ እንኳ የሚያነሳሱህን ግቦች አስቀምጥ፡፡ በቀላሉ ልታሳካው የምትችለውን ግብ ካስቀመጥክ ከአቅምህ በታች የሆነን ነገር የማሳካት እድልህ ከፍተኛ ነው፡፡ ሌስ ብራውን በጥልቀት እንዳስቀመጠው “ለጨረቃዋ ዓልም፣ ጨረቃዋን ብትስት እንኳ ከከዋክብቶቹ መሀል አንዷ ላይ ትቆማለህ፡፡” 

ስራን ከመስራት ውጭ ወደ ስኬት፣ ወደ ደስታ ወይም ወደ ጤና የሚያደርስ ሌላ ምንም ምስጢር የለም፡፡ ትርጉም ያለው ግብን ለመከተል ስላለህ ፍላጎት ፍቃድንም ሆነ ይቅርታን አትጠይቅ - ዝም ብለህ ግብህን ተከትለህ ተጓዝ፡፡ በችሎታዎችህ ላይ ተመካ፤ እንዲሁም ውድቀት አማራጭ ይሆናል ስለሚለው ሀሳብ ፍንጭ አይኑርህ፡፡ እየሄድክ ተማር፡፡ ከወደቅክም ወደፊት ውደቅ፡፡

በርታ ለጨረቃዋ አልመህ ተጓዝ… ባይሳካልህ እንኳን ከዋክብቱ ላይ ታርፋለህና!
 
#የስኬት_አቡጊዳ መጽሐፍ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence