Get Mystery Box with random crypto!

መመሰጥ-ግስታልት ቴራፒ የብዙዎቻችን ሕይወት በተግባራት የተጨናነቀ እና ፋታ አልባ ነው፡፡ ጸጥ ማ | የስብዕና ልህቀት

መመሰጥ-ግስታልት ቴራፒ

የብዙዎቻችን ሕይወት በተግባራት የተጨናነቀ እና ፋታ አልባ ነው፡፡ ጸጥ ማሰኘት የማንችለው ብዙ ጫጫታ አለ፤ መተንፈስ እስከሚያዳግተን ድረስ እንጨነቃለን፡፡ እንቅልፍ ርቆናል፡፡ ሕይወታችን አሁንም ድፍርስ ነው፤ መስከን አንችልም፡፡ ለብቻችን የምንሆንበት ጸጥ ያለ ቦታ ያስፈልገናል።ይህ ነው የግስታልት ቴራፒ ተብሎ የሚጠራው።

ግስታልት ቴራፒ መነሻውን ያደረገው “አሁንን ብቻ ኑር” ከሚል የህላዊነት እሳቤ ነው፡፡ ዓለምን ያለምንም ጣልቃ ገብ ሃሳብ ቅመሳት። ያለፈ ታሪክ፣ የነገ ስጋትህን ሁሉ ለአፍታ ዘንጋቸው፡፡ ሸክምህን ሁሉ አራግፍ᎓᎓ አሁንን ብቻ በጸጥታ ውስጥ ሆነህ ኑረው፡፡ አሁን ላይ ብቻ አተኩር። ይህ ሳይኮሎጂስቶች የሚጠቀሙበት ቴራፒ (ህክምና) ነው ለጥቂት ደቂቃዎች ራስህን ከዓለም ለይተህ ጸጥ ባለ ስፍራ ሁን ምንም አታስብ ... ምንም አትስራ፡፡

ከዚህ ቀደም የነበረህ ማንነትህ አሁንህን ይጫነዋልና እርሳው᎓᎓ ሆነ ጭምትነትህ ያለፉ ድህነትህ፣ ኃብትህ... ተጫዋችነትህም ማንነቶች ናቸው፡፡ ወደ ኋላ መመለስ የለብህም። እኔ እንዲህ ነኝ ብለህ የምታስበውን ሁሉ እርሳ።

ይህ የባዶነት ስፍራ Fertile void ይሰኛል። ልክ ዘርን እንደሚሰጥ እርሻ ያልታረሰ ባዶ ስፍራ፡፡ በዚህ ስፍራ ያለኸው እንዲደብርህ ወይም ከራስህ ጋር እንድታወራ አይደለም። ልክ እንደማብሪያ ማጥፊያ መብራት እንደሚያጠፋ፣ ልክ በር ከውጪኛው ዓለም እንደሚለይህ ወይም ሰው ሲረብሽህ “እሽሽ” እንደምትልበት አይነት ... ይህም የጨለማ እና የባዶነት ስፍራ ነው። ሁሉንም ነገር ታጠፋለህ፣ ትዘጋለህ።

ሃሳቦችህ ባንተ ታዘው ሳይሆን በራሳቸው ይፈሳሉ፡፡ ላንተ ማሰብ አልተፈቀደምና የሃሳብ ወንዙን ዳር ሆኖ ከመመልከት ውጪ መሟገት አልያም ከወንዙ ጋር ትግል መግጠም አትችልም።

ይህ የባዶነት ስፍራ አዳዲስ እና ያላስተዋልካቸው ሃሳቦች ከህቡዕ ህሊናህ ወደ ውጭ የሚፈሱበት ስፍራ ነው፡፡ ይህ ስፍራ ልክ እንደ ለም መሬት ፍሬን ያፈራል፡፡
በባዶነት ስፍራ ውስጥ መሆን በእጅጉ ይከብዳል፡፡ ልክ አለቃ ስራ ሲያዝህ አልሰራም የማለትን ያህል ይከብዳል፡፡ ከዚህ ቀደም አልለመድከውምና አዙሪትህን መስበር ቀላል አይሆንልህም:: ሆኖም ራስህን በባዶነት ስፍራ መሆንን አላምደው፡፡ ምንም አለማሰብ፣ ምንም
አለማድረግ፣ ከማንም ጋር አለመሆን... ባዶነት

ፍሉይ አለም

@Zephilosophy
@Zephilosophy