Get Mystery Box with random crypto!

ሶሪያዊዉ ጋዜጠኛ በአገሩ ፍርስራሽ ለይ ቆሞ አገራቸውን ከማፍረሳቸው በፊት  የነበረውን ሁኔታ መለስ | የስብዕና ልህቀት

ሶሪያዊዉ ጋዜጠኛ በአገሩ ፍርስራሽ ለይ ቆሞ አገራቸውን ከማፍረሳቸው በፊት  የነበረውን ሁኔታ መለስ ብሎ በምሬት እያስታወሰ  እንዲህ በእንባው ጻፈ :-"

" ተከፋፍለን ነበር። እንጨቃጨቅ ፤ እንከራከር ፤ እንጣላ  ነበር።  መንፈሳዊ እሴቶች ወድቀው ነበር። ማናችንም ለማናችንም ግድ አልነበረነም።

"ሌሎች ደግሞ  ራሳቸውን ገለልተኛ አድርገው በሩቅ ቆመው ያዩን   ነበር።  ሌሎችም በእለት ሕይወታቸው ለይ ተጠምደው ነበር። ማንም እያስተዋለ አልነበረም።

" ይኸ ሂደት እያደረ ጠነከረና ቀዳዳ ሲያገኝ ድንገት ፈነዳና አገራችንን በሁላችንም ለይ አፈረሳት። አገራችን አይናችን እያየ ሳናስበው ድንገት  ፊታችን  ለይ  ነደደች።

"ያኔ ታዲያ ማናችንም በሰአቱ አገራችንን በማፍረስ ሂደት ለይ  እንደነበርን አላስተዋልንም ነበር። አገራችን መፍረሷን ያወቅነው አገራችን በሁላችንም ለይ ፈርሳ ሲጨልምብን ነበር.........።

"በወቅቱ አለን አለን ሲሉ የነበሩ የየቡድኑን መሪዎችን ጨምሮ ሕጻናትና እናቶችን ሳይምር በወቅቱ  ገለልተኞች የነበሩትን ሳይለይ አገራችን ሁላችንንም በፍረስራሿ ለይ ቀበረችን። ። " እያለ ይቀጥላል።

ዛሬ ሶሪያውያኑ አገራቸውን ዳግም ማግኘት ይፈልጋሉ። አላገኟትም ። የለችምና !!

ልብ ያለው ልብ ይበል

via-Wondwosen seifu

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence