Get Mystery Box with random crypto!

ትወድቃለክ አትወድቅም እሱ ጥያቄ አይደለም!!! ሁሉም ይወድቃሉ ጥያቄው ግን ትነሳለክ ወይንስ እዛው | ይቻላል የፊልም እና የቴአትር ቡድን💪

ትወድቃለክ አትወድቅም እሱ ጥያቄ አይደለም!!! ሁሉም ይወድቃሉ ጥያቄው ግን ትነሳለክ ወይንስ እዛው ትቀራለክ ነው!!!! ጀግና ጀግንነቱ የሚታየው በፈተና እና በመሠናክል መሃል አልፎ ያለመው ላይ መድረስ ሲችል ነው!!! አንዳንዴ መውደቃችን ለመልካም ነው ብለን አስበን! ነገ መልካም እንደሚሆን ለልባችን ደጋግመን በመንገር ሃይላችንን ጨምረን ከወደቅንበት እንነሳ! ዛሬ ለነገ መሠረት ናት!!! ሰው ካስቀየምን በይቅርታ እናልፈዋለን! ሰው ከደከመ አይዞክ ብለን ለማበርታት እንሞክራለን! ታዲዬ ለእኛስ ያለ እኛ ማን አለን!!! ከሰውነታችን በላይ አህምሯችን እንዳይደክም ብርታትን እንስጠው! ከደከመ ከወደቀ ደግሞ ልባም እንደሆነ እና ማንም ከሚለው በላይ ጀግና እንደሆነ ለራሳችን ደጋግመን በመንገር ብርታትን እንስጠው!!! ምክንያቱም ላንተ ካንተ የቀረበ ማንም የለህምና!!!
ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው።
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal