Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.83K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2024-04-02 09:29:11
በፒያሳና አካባቢው እየተከናወነ ባለው የመንገድ ግንባታ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መንገዱ ስለተዘጋ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

ቀደም ሲል የመንገዱን መዘጋት በተመለከተ መረጃ ቢሰጥም አሁንም አሽከርካሪዎች ወደ ግንባታ ቦታው እየመጡ በግንባታ ስራው ላይ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም በፒያሳና አካባቢው የመንገድ ግንባታ እየተከናወነ በመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ መንገዱ ስለተዘጋ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ በማለት አሳስቧል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• ከጊዮርጊስ አደባባይ በእሳት አደጋ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከቅድስተ ማርያም ወደ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

• ከአራት ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከባሻ ወልዴ ችሎት ወደ ቱሪስት እና ወደ ቅድስተ ማርያም

• ከእሪ በከንቱ (ቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም) ወደ ደጎል አደባባይ እንዲሁም

• ከደጎል አደባባይ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ በሚወስዱት መንገዶች መግባት እና መንገዶቹን ለጊዜው መጠቀምም ሆነ በመንገዶቹ ላይ መኪና ማቆም እንደማይል ተገልጿል፡፡

ይህን በመመገንዘብ አሽከርካሪዎች ከእነዚህ ውጪ ያሉ ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
16.3K views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 08:48:18 መንግስት ‘’የመንግስት ሰራተኞች እንዲደራጁ’’ የሚከለክለውን አዋጅ እንዲያሻሽል ተጠየቀ፡፡

የኢትየጵያ መንግስት፤ የመንግስት ሰራተኞች እንዲደራጁ አለመፍቀዱ ሰራተኞቹ ህብረት ፈጥረው መብታቸውን እንዳያስከብሩ አድርጓቸዋል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ በአለም ስራ ድርጅት በኩል የወጣውን አለም አቀፍ ስምምነትን በሚቃረን መንገድ  በአሰሪና ሰራተኛ አዋጇ የመንግስት ሰራተኞች ተደራጅተው ስለመብታቸው እንዳይጠይቁ መከልከሏ ተነግሯል፡፡

ይህም ለወራት ደመወዝ ያልደረሳቸውን ጨምሮ፣ በከፍተኛ የገቢ ግብር እና በመሰል ችግሮች የሚንገላታው የመንግስት ሰራተኛ ተደራጅቶ እና ህብረት ፈጥሮ ስለ መብቱ  እንዳይከራከር እንዳደረገው ተጠቅሷል፡፡

ይህንን ለሸገር የነገረው የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን(ኢሰማኮ) ነው፡፡

በኢትዮጵያ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ፤ የመንግስት ሰራተኞች የመደራጀት መብት ስለሌላቸውና የማህበሩ አባል መሆን ስለማይችሉ፤ ሰራተኞቹ  ስለሚደርስባቸው የመብት ጥሰት መከራከርም ሆነ መታገል አልቻልንም ሲሉ የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዚደንት ካሳሁን ፎሎ ለሸገር አስረድተዋል፡፡

ምንም እንኳ የኢትዮጵያ መንግስት ሰራተኞቹ እንዲደራጁ ይከልክል እንጂ፤ ይህንን የመንግስት ሰራተኞች እንዲደራጁ የሚፈቅደውና በዓለም ስራ ድርጅት  በኩል የተደነገገውን ስምምነት ኢትዮጵያ ፈርማለች፡፡

በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀፅ 13 መሰረት ደግሞ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸው ሰነዶችና ስምምነቶች የሀገሪቱ ህግ አካል ሆነው እንደሚቆጠሩ ይደነግጋል፡፡

በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ የፈረመችውን ስምምነት አክብራ፤ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጇን እንድታሻሽል በየጊዜው መንግስትን እንየጠየቅን ነው ብለውናል የኢሰማኮ ፐሬዚደንት፡፡

ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት የፈረመቸው ነገር ግን የተፈፃሚ ያላደረገችው፤ ይህንን የመንግስት ሰራተኞች የመደራጀት መብትን በተመለከተ በዓለም ስራ ድርጅት በተደጋጋሚ እየተከሰሰችና እየተጠየቀች እንደሆነም  አቶ ካሳሁን አንስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ አሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት መደራጀት የሚችሉት በግል እና በመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩት ብቻ ናቸው፡፡

ከአፍሪካ ሀገራት፤ የመንግስት ሰራተኞችን እንዳይደራጁ የከለከሉት ኤርትራ፣ ጅቡቲ እና ኢትዮጵያ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/yc3vn754

ማንያዘዋል ጌታሁን
ሸገርን ወሬዎች
15.6K views05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-01 22:33:22
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ108 ሺህ እስከ 305 ሺህ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ " እስካሁን አልመለሱልኝም " ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶግራፍ ይፋ አደረገ።

ወደዚህ እርምጃ ከመግባቱ በፊት በተደጋጋሚ ማስጠንቀቁን አስታውሷል።

በዚሁ መሠረት እስካሁን ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ ይፋ ማድረጉን ገልጿል።

አሁንም ለመጨረሻ ጊዜ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም የተራዘመውን የገንዘብ መመላሽ ዕድል ተጠቅመው ገንዘብ ያልመለሱ እንዲመልሱ አስጠንቅቋል።

በተሰጠው የጊዜ ገደብ የማይመልሱትን ወደ ህግ እንደሚያቀርብም ገልጿል።

https://combanketh.et/list-of-customers/?fbclid=IwAR2ZWAndWBR1lt_ytwfDL9IiTYrml76PgdWo_FBhLxRRMTF01VxzN1ekfKA
16.7K views19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-01 16:06:25
መጋቢት 23፣2016
 
በአዲስ አበባ እንዲሁም የበልግ አብቃይ በሆኑ የሀገሪቱ ክፍሎች በመጪዎቹ ቀናት  ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር ተነገረ፡፡

https://tinyurl.com/4k9umr3y

ምህረት ስዩም
18.3K views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 13:44:45 አዲስ አበባ እንደ አዲስ በሚባል ደረጃ ፈርሳ እየተገነባች ነው

መንግስት ‘’አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ የማድረግ ቃል ከ5 ዓመት በፊት ገብቻለው፤ የአሁኑ ስራ እሱን ወደ ተግባር የመቀየር ነው’’ ይላል፡፡

ስራው ደጋፊም ነቃፊም አላጣውም፡፡

ከሚነሱት ጥያቄዎች አንደኛው ከህግ ድጋፍ ጋር የተገናኘ ነው፡፡

ለአንድ ዙር ሀገር እንዲያስተዳድር የተመረጠ ፓርቲ በዘላቂነት የከተማን ቅርፅ የሚቀየር ስራን የመስራት የህግ ድጋፍ አለው ወይ?





የኔነህ ሲሳይ
14.6K views10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 13:43:34 አዲስ አበባ መልሳ ልትገነባ ፈራርሳለች

እዚህም እዚያም መንገድ ፣በመንገድ ላይ የተተከለው ዛፍ፣ የንግድና የመኖሪያ ቤት፣ ህንፃውና አጥሩ ሳይቀር ወደ ፍርስራሽነት ተቀይሯል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ሀላፊ ከሰሞኑን ሸገር ስቱዲዮ ተገኝተው ስለ ጉዳዩ ሲያብራሩ ለተነሺዎች ከ7 ወር በፊት መረጃ ሰጥተናል፤ በተለያየ ምክንያት ያልሰሙ ካልሆኑ በስተቀር ሌሎቹ ስለ ጉዳዩ በቂ መረጃ ነበራቸው ሲሉ መልሰዋል፡፡

መንግስት አስቤና መክሬ ስራውን ጀመርኩኝ ቢልም የሚታየው ግን ከዛ የተለየ ነው፡፡

በቅርብ ጊዜ ውስጥ የተገነቡ፣ ከቀናት በፊት የተተከለው፣ የተገነባና የተቀባው ሁሉ ዛሬ ፍርስራሽ ሆኗል፡፡

ይህ በኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ምንድነው?

የእለት ጉርሱን ተሯሩጦ የሚያገኘው ኢ-መደበኛ ስራ ላይ የተሰማራው የከተማው ህዝብስ በዚህ የማፍረስ መገንባት፣ የመኖሪያ ቦታውን የመቀየር ሒደት ምን ያህል ተጎጂ ነው?





ተህቦ ንጉሴ
13.9K viewsedited  10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 13:07:25
የአዲስ አበባ የከርሰ ምድር ውሃ እየተሟጠጠ መሆኑን ጥናት አመለከተ

የአዲስ አበባ የከርሰ ምድር ውሃ እየተሟጠጠና በመዲናይቱ የውሃ አቅርቦት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ በዚህ ሳምንት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ የምህንድስና ባለሙያዎች ያቀረቡት ጥናት ማመልከቱን ሪፖርተር ዘግቧል።

መዲናይቱ በአሁኑ ወቅት በቀን 1.2 ሚሊዮን ኪውቢክ ሜትር የውሃ ፍላጎት እንዳላት ሲገለፅ ነገር ግን የውሃ አቅርቦቱ 40 በመቶ የሚሆነውን ፍላጎት ብቻ እየሸፈነ ስለመሆኑ ተመላክቷል። የከተማዋ የውሃ ፍላጎት ከአቅርቦት በላይ መሆኑ የውሃ ጥራት እንዲኖር አድርጓልም ተብሏል።

ቁጥጥር ያልተደረገበት የከርሰ ምድር ውሃ አጠቃቀም እንደሚስተዋል ጥናቱ ሲጠቁም የውሃ ማጠራቀሚያ ታንኮች ላይ ጥገኛ መሆን ችግሩን እያባባሰው እንደሆነ ተጠቁሟል። ይህንን ለመቅረፍ የዝናብ ውሃን ለማከማቸት የሚረዱ ማጠራቀሚያዎችን መገንባት እንደሚገባና መንግስትም የውሃ ቁፋሮ እና የከርሰ ምድር ውሃ አጠቃቀምን የተመለከቱ ጠንካራ ህጎች ማውጣት እንዳለበት ባለሙያዎቹ አሳስበዋል።

@TikvahethMagazine
13.4K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 12:57:00
የሀገራችን የቁልቁለት መንገድ

ኢትዮጵያ ውስጥ መማር በእውቀቴ የተሻለ ቦታ ደርሳለው ማለት ትርጉም ያጣበት ወቅት
13.1K views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 07:21:52 አጎት ባልቻ

እስቲ ዛሬ ትንሽ ስለ አጎት ባልቻ እንጨዋወት። ጽሁፉን ከዚሁ ሰፈር ማግኘቴን ከወዲሁ ልንገራችሁ። ነገር ግን ወሬ ጨማምሬበት ኢትዮጵያዊ ቃና እንዲኖረው አድርጌያለሁ።

ለመሆኑ አጎት ባልቻ ማን ናቸው?! አትቸኩል፣ ልነግርህ ነው። አጎት ባልቻም እንዲሁ እንዳንተ ችኩል ነበሩ።

አጎት ባልቻ ለ40 ዓመታት ያህል አሜሪካን አገር ከኖሩ በኋላ፣ በ70 ዓመታቸው ወደ አገራቸው ተመለሱ። በያዝነው ዓመት ነው ባለ 5 መኝታ ቤት የተንጣለለ ቤታቸው ውስጥ መኖር የጀመሩት። የቤት መስሪያ ገንዘብ ለመቆጠብ ድፍን 30 ዓመታትን ፈግተዋል። ቤቱን ለመገንባት ደግሞ 10 ዓመታትን።

የአጎት ባልቻ ቤት የተንጣለለ ባለ ሶስት ወለል ቪላ ነው። አምስት ቅንጡ መኝታ ቤቶች ያሉት ሲሆን፣ ሁሉም መኝታ ቤቶች የሚገኙት ከሁለተኛ ወለል ጀምሮ ነው። በተለይ ግዙፉ እና ቅንጡ ዋና መኝታ ቤት የሚገኘው ሶስተኛ ወለል ላይ ነው። ከታች ያሉ ከፍሎች ሳሎን፣ ወጥ ቤቶች እና የእንግዳ መጸዳጃ ቤት ናቸው።

አጎት ባልቻ አሁን የሚኖሩት ከታች ባለው የቤቱ ሳሎን ውስጥ ነው። ምክንያቱም የ70 ዓመቱ አዛውንት ያለ ሌላ ሰው እርዳታ ደረጃውን መውጣት አይችሉም። በሰው እርዳታም ቢሆን ቢያንስ 10 ደቂቃ ይፈጅባቸዋል። ለዚህ ነው ሳሎን ውስጥ ለመኖር የወሰኑት። ቅንጡ እና ዋና መኝታ ቤታቸው ውስጥ የቤት ሰራተኛቸው እንድትተኛ ፈቀዱ።

አጎት ባልቻ የጡረታ ኑሮአቸው እንደዚህ ይሆናል ብለው የገመቱ አይመስልም። ተጨባጭ እውነታ ግን ይሄው ነው። አጎት ባልቻ አስደሳች የሚባል ህይወት የላቸውም። የፈለጉትን ምግብ መመገብ ብቻ ሳይሆን የፈቀዱት መኝታ ቤት ውስጥ እንኳን መተኛት አይችሉም።

እና በውጭ አገር እየኖርህ ቤት የምትገነባ ወዳጄ፣ ቤቱ ግፋቢል ከ50 ዓመትህ በፊት ተሰርቶ የማያልቅ ከሆነ እርሳው። እንደ አጎት ባልቻ 40 ዓመታትን አታባክን። በፍጹም ከጡረታ በኋላ እኖራለሁ ብለህም አታስብ፤ ከጡረታ በኋላ ህይወት የለም። አሁኑኑ በመሃል በመሃል ጡረታ እየወጣ ተዝናና።

በአጎት ባልቻ ስም ጧ ያለ እንቅልፍ ተመኘሁልህ።
Lami S
14.5K views04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-29 23:54:39 #NewsAlert በአዲስ አበባ ከተማ እየተስፋፋ የመጣው የእገታ ወንጀል

ከሰሞኑ በስፋት እየደረሱኝ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በፊት በፊት በክፍለ ሀገራት፣ ከዛም በአንዳንድ የአዲስ አበባ አቅራቢያ ስፍራዎች ሲከናወኑ የነበሩ የእገታ ወንጀሎች አሁን ላይ በአዲስ አበባ ከተማ መታየት ጀምረዋል።

ከ10,000 ብር ጀምሮ እስከ 1 ሚልዮን ዶላር የተጠየቀባቸው ሰዎች እንዳሉ፣ እገታዎቹ በቀንም ይሁን በጭለማ እንደሚከናወኑ፣ አብዛኞቹ የፀጥታ አካላትን በመምሰል (ወይም ሆነው... ይህ ሲጣራ ይታወቃል) ድርጊቱን እንደሚፈፅሙ እና ከመኖርያ ቤታቸው ጭምር የተወሰዱ ሰዎች እንዳሉ አረጋግጫለሁ።

እንደ ነጋዴዎች፣ ዲያስፖራዎች እና የውጭ ዜግነት ያላቸው ሰዎች እና ብር አላቸው ተብለው የሚገመቱ ማንኛውም ሰዎች በተለይ ኢላማ እንደሆኑ ታውቋል።

አጋቾቹ ድርጊቶቹን ከፈፀሙ በኋላ ታጋቾች ድርጊቱን ለፖሊስ እንዳያሳውቁ ስለሚያስፈራሩ ትክክለኛ የድርጊቱን መጠን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው።

ማስተባበል መቼም መፍትሄ ስለማይሆን አሁንም ሳይረፍድ የሚመለከተው አካል በይፋ ወደፊት በመምጣት ድርጊቱን ቢያንስ በይፋ ለህዝብ ማሳወቅ አለበት።

ከእንዲህ አይነት እገታ 'ተጠንቀቁ' ቢባል እንዴት መጠንቀቅ እንደሚቻል ባላውቅም... ብቻ ጥንቃቄ አይለየን።

@EliasMeseret
15.0K views20:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ