Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.66K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-11 22:36:04 መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያሥገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለባለ ዕድለኞች በዕጣ አስተላልፏል።

በዕጣ የተላለፉት አጠቃላይ 1,336  የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፦
- ባለ 4 መኝታ
- ባለ 3 መኝታ
- ባለ 2 መኝታ
- ባለ 1 መኝታ ናቸው።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ለሠራዊት አባላት እና ቋሚ ለሆኑ ስቪል ሰራተኞች ነው የተላለፉት።

(የቤት ባለዕድለኞች ስም ዝርዝር ከላይ በPDF ተያይዟል)

#FDREDefenseForce
15.8K viewsedited  19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-11 18:25:03
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለባለ ዕድለኞች በእጣ ያስተላልፋል።

ፋውንዴሽኑ ከዚህ በፊት ተመዝግበውና ቆጥበው መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ የሠራዊት አባላትና ስቪል ሠራተኞች 1236  ቤቶችን በእጣ አስተለልፎ ነበር።

ዛሬ ደግሞ 1336 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በእጣ ያስተላልፋል ተብሏል።

#FDREDefenseForce
17.4K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-09 21:46:00 #ጎጆብሪጅ #ጤናባለሙያዎች

" ውላችን ይቋረጥ ፣ #ገንዘባችንም_ይመለስልን ብለው የፈረሙ 4,000 ቆጣቢዎች አሉ " - የቤት እጣ ቆጣቢዎች

" ከጤና ሚኒስቴር፣ ከዳሽን ባንክ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " - ጎጆ ብሪጂ

ከ7 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ #የጤና_ባለሙያዎች ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከዳሽን ባንክ የሦስትዮሽ ውል የፈረመው ጎጆ ብሪጂ ሀውሲንግ ፦
እጣውን በወቅቱ እያወጣ ባለመሆኑ፣
እጣ የወጣላቸውም ግንባታ ባለመጀመሩ፣ 4,000 ቆጣቢዎች ገንዘባቸው እንዲመለስ ቢጠይቁም እንዳልተመለሰላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አሁንም ቢሆን ገንዘቡ እንዲመለስላቸው ጠይቀዋል።

የቆጣቢዎቹ ኮሚቴ በጉዳዩ ዙሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " በየሶስት ወሩ ለማውጣት እጣው ሳይሰጥ 2 ዙር አልፏል። ለምን ? ተብለው ሲጠየቁ ' #የመሬት_አስተዳደር_ችግር_ስላለብን_ነው ' እያሉ እስካሁን ቆዩ " ብሏል።

" ውላችን ይቋረጥ ፤ ገንዘባችንም ይመለስልን ብለው የፈረሙ 4,000 የቤት ቆጣቢዎች አሉ " ሲል የገለጸው ኮሚቴው በደብዳቤ ጭምር ቢጠይቅም መፍትሄ እንዳልተሰጠው አስረድቷል።

ለተነሳው የቤቶች እጣ መዘግየት ቅሬታ በ ' ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ ' በኩል ምላሽ እንዲሰጡን የተጠየቁት አቶ አልማው ጋሪ ፤ " የገጠመን ችግር በአደረጃጀት ላይ #መዘግየቶች ስለነበሩ ነው " ብለዋል።

" የሚያደራጀው የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን የሚባለው ነው " ያሉት አቶ አልማው፣ " ሌላ ሳይት ላይ በተፈጠረ ክስ ትንሽ ሥራው ስለቆመ እስኪ ውጤቱን እንየው የሚል ሀሳብ ተነስቶ ስለነበረ የመዘግየት ጉዳይ አጋጥሟል " ነው ያሉት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የቤት ቆጣቢዎቹ ከጠየቁ ለምን ገንዘባቸውን አልመለሳችሁም ? ሲል ላቀረበው ጥያቄ ፣ " ውሉ የሚያስቀምጣቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ይህን ደግሞ ለብቻችን ሳይሆን ከጤና ሚኒስቴርም ከዳሽን ባንክም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " ብለዋል።

" የመጀመሪያው እጣ ማውጣት ተደርሶ ወደ 300 ሰዎች እጣ የደረሳቸው አሉ። እነርሱን ለማደራጀት በሂደት ላይ ነው ያለነው " ያሉት አቶ አልማው " አንዳንዶች ደግሞ ቅሬታ አላቸው እየመጡ ይጠይቃሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

" የቅሬታ አቅራቢዎቹን ጉዳይም ባለፈው ሳምንት ጤና ሚኒስቴር የተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ውይይት ተደርጎ አቀረቡ አቅጣጫ ተቀምጧል። ምናልባት በዚህ ሳምንት አንድ ደረጃ ላይ ይደርሳል " ብለዋል።
14.3K views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-09 21:45:19
13.6K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-09 05:55:28
የቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም ለሊት 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ ፣ የኬሮሲን ፣ የአይሮፕላን ነዳጅ ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #ባለበት_እንደሚቀጥል አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

- ነጭ ናፍጣ ብር 79.75 በሊትር
- ኬሮሲን ብር 79.75 በሊትር
- የአውሮፕላን ነዳጅ ብር 70.83 በሊትር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ ብር 62.36 በሊትር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ ብር 61.16 በሊትር ሆኖ ባለበት ይቀጥላል።

የቤንዚን ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጎ በሊትር 78 ብር 67 ሳንቲም ገብቷል።
@tikvahethiopia
17.8K views02:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 15:46:42 ካሳር ቤት እስከ ወሎ ሠፈር ለኮሪደር ልማት ፕሮጀክት 3,250 አባወራዎች ይነሳሉ

ከፒያሳ በመነሳት በሳር ቤት በኩል እስከ ወሎ ሠፈር ድረስ የሚገነባው አዲሱ የኮሪደር ልማት፣ 3,250 አባወራዎችን ወይም ከ14 ሺሕ በላይ ሰዎችን እንደሚያስነሳ ተመላከተ፡፡ ተነሺዎችን ለማስፈር 21 ሔክታር መሬትና ስድስት ቢሊዮን ብር የካሳ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ታውቋል፡፡

ከአሥር ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ ከፒያሳ በመነሳት እስከ ብሔራዊ፣ ከብሔራዊ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ሳር ቤትና ከሳር ቤት እስከ ወሎ ሠፈር ተብሎ በአምስት ንዑስ ፕሮጀክቶች ተከፋፍሎ ዲዛይን እንደወጣለት ሪፖርተር የተመለከታቸው የዲዛይን ዶክመንቶች ያሳያሉ፡፡ አጠቃላይ ፕሮጀክቱ አምስት ክፍላተ ከተሞችን የሚነካ ሲሆን እነዚህም አራዳ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ ንፋስ ስልክና ቦሌ ናቸው፡፡

ጠቅላላ ፕሮጀክቱ 460 ሔክታር መሬት ይዞታ የሚነካ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 114 ሔክታር ለመልሶ ማልማት ነፃ እንደሚደረግ ዶክመንቱ ያሳያል፡፡

ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም 40 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ለአብነት ያህል ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ለፈጣን የአውቶቡስ መስመር ግንባታ ይውላል፡፡ ስድስት ቢሊዮን ብር ለማኅበራዊ ቤቶች ግንባታ፣ ስድስት ቢሊዮን ለተነሺዎች ካሳ ክፍያ፣ አራት ቢሊዮን ብር ለመንገድ ግንባታ፣ ሦስት ቢሊዮን ለፓርክ (Green Park) ተመድቧል፡፡ በተጨማሪም የፓርኪንግ ቦታዎች፣ ሰባት ያህል ድልድዮች፣ የመሠረተ ልማትና የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች ይገነባሉ፡፡

ወጪ የሚደረገውን 40 ቢሊዮን ብር በአምስት ዓመታት ውስጥ በእጥፍ ለማስመለስ መታቀዱንም ሰነዱ ያመለክታል፡፡ በኮሪደር መስመሩ ላይ መንግሥት 114 ሔክታር መሬት ነፃ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን፣ ይኼንን መሬት 70 ሺሕ ብር በካሬ ለአልሚዎች በማከራየት በአምስት ዓመት ውስጥ 99 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ዶክመንቱ ያሳያል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በዚህ መስመር ላይ መንግሥት ሊያከራያቸው ካቀዳቸው የመኖሪያ፣ የንግድና የቢሮ ሕንፃና ቤት ከ5.8 ቢሊዮን ብር በላይ በየዓመቱ ገቢ ለማስገኘት መታቀዱ ታውቋል፡፡ ከፒያሳ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ አብዛኛው ቦታ ለአረንጓዴ ልማት ማለትም ለሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ታቅዷል፡፡ አምባሳደር አካባቢ ያለው የመከላከያ ሚኒስቴር ግቢ ሙዚየም፣ ካፌና መዝናኛ የሚኖረው የባህል ማዕከል እንደሚቀየር ዲዛይኑ ያሳያል፡፡

የሰይጣን ቤት ተብሎ የሚታወቀው ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ ያለው ቦታ ወደ ባህል ማዕከልና መዝናኛ ቦታ በመጠነኛ ለውጥ ያደርጋል፡፡ ከአፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት ያለው 1.2 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ‹‹የአፍሪካ ማዕከል›› ለመገንባት ይውላል፡፡ ማዕከሉ ሙዚየም፣ ላይብረሪ፣ የባህልና መዝናኛዎች ሲኖሩት አጠቃላይ አካባቢው ከፍተኛ ጥበቃ ያለው የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አገልግሎት ይቀየራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከሜክሲኮ ሳር ቤት ባለው ንዑስ ፕሮጀክት ከታሰቡት ብዙ ዕቅዶች ውስጥ ሆስፒታልና አዲሱ ቱሞሮ (Adisu Tomorrow) ልዩ የኢኮኖሚ ዞንም ይገኝበታል፡፡ በዚህ አካባቢ ከአራት ወለል ሕንፃ (G+4) በታች የሆኑ ሕንፃዎች ሁሉም ይፈርሳሉ፡፡ የኮሪደር ልማቱን ለማስፈጸም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሜጋ ፕሮጀክቶች ጽሕፈት ቤት፣ የከተማ አስተዳደሩ፣ የአዲስ አበባ ዕቅድና ልማት ኮሚሽንን ጨምሮ ሃያ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ ethiopianreporter
13.1K viewsedited  12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 15:46:37
12.8K views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-05 20:19:49
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያሥገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ እንደሚያሥተላልፍ አሥታወቀ።

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያሥገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንቦት 03 ቀን 2016 ዓ.ም በእጣ እንደሚያሥተላልፍ የፋውንዴሽኑ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ደርጃ መገርሳ በዛሬው ዕለት አሥታውቀዋል።

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን 128 ባለ አራት መኝታ 260 ባለ ሦስት መኝታ 480 ባለ ሁለት መኝታ 220 ባለ አንድ መኝታ በድምሩ 1088 ቤቶችን በቃሊቲ እንዲሁም 128 ባለ አራት መኝታ 120 ባለ ሦስት መኝታ በድምሩ 248 ቤቶችን በኮዬ ፈጩ በአጠቃላይ ድምር 1336 ቤቶችን ግንቦት 03 ቀን 2016 ዓ.ም በእጣ እንደሚያሥተላልፍም ብርጋዲየር ጄኔራል ደረጀ ገልፀዋል።

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ምክትል ሥራ አሥፈፃሚና የቤቶች ግንባታና ማሥተላለፍ ሃላፊ ኮሎኔል ታደሠ ጌታቸው በበኩላቸው በእጣ በሚተላለፉት የጋራ መኖሪያ ቤቶች 1125 ከሠራዊቱ የተሠናበቱ፣ 6033 በሥራ ላይ ያሉ የሠራዊት አባላት 539 ሲቪል ሠራተኞች በድምሩ 7,697 በእጣ የሚካተቱ መሆኑንም ተናግረዋል።

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን በእጣ ከሚያሥተላልፋቸው ቤቶች በተጨማሪ 440 ቤቶች በመቀሌ 312 ቤቶች በባህርዳር 232 ቤቶች በሃዋሳ በድምሩ 984 ቤቶችን እያሥገነባ እንደሚገኝ የገለፁት ኮሎኔል ታደሠ ጌታቸው በአዲስ አበባ ከተማ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 1024 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን አሥገንብቶ ለሠራዊቱ ለማሥተላለፍ የመሠረተ-ድንጋይ መቀመጡንም አሥረድተዋል።

በ2016 ዓ.ም ጥር ወር ድረስ አራት እርከን የደረሱ ሲኒዬር ኮሎኔሎችና ጄኔራል መኮንኖች ሙሉ በሙሉ ያለ እጣ የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ተገልጿል።

ዘጋቢ ውብሸት ቸኮል
ፎቶግራፍ ምስጋናው ከበደ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
14.9K views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-02 22:44:03
በአዲስ አበባ ከተማ የወጣው የመሬት ሊዝ  ጨረታ ተራዘመ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ  ፤ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ በሌሎችም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል።

በዚህም ከሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 24/2016 ዓ/ም ድረስ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ሲከናወን ቆይቷል።

ነገር ግን የጨረታ ሰነድ ሽያጩ ከ28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት መራዘሙ ተነግሯል።

ተጫራቾች ፦
- የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣
- ሲፒኦ፣
- የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣
- ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበት ስሊፕ
- ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉ እና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በኤንቨሎፕ በማሸግ ግንቦት 09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ተብሏል።

ጨረታው ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 12/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 9 የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ  እንደሚከፈት ተገልጿል።

የጨረታው ዝርዝር
https://t.me/tikvahethiopia/87112

@tikvahethiopia
15.0K views19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-01 18:32:39
ፒያሳ
14.8K views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ