Get Mystery Box with random crypto!

🦋Ľĭ£€🦋

የቴሌግራም ቻናል አርማ hiwotlife — 🦋Ľĭ£€🦋 Ľ
የቴሌግራም ቻናል አርማ hiwotlife — 🦋Ľĭ£€🦋
የሰርጥ አድራሻ: @hiwotlife
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 248
የሰርጥ መግለጫ

Hey Guys Join my new channel it's all about LIFE😔😂❤️😭😱

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-25 10:50:56 ትንሽ ብርሀን

እግዜር ሆይ ትንሽ ብርሀን ብትሰጠን
ጨለማው ለከት ስላጣ÷ ስሌለው መጠን።

ትንሽ ብርሀን÷ አለ አይደል
ሚያወጣን÷ መንገዱ ከጠፋን ከጨለማው ገደል።
ትንሽ ብርሀን ÷ ለተስፋ እንዲሆነን
አለዚያማ
ተስፋ በሌለበት ÷ መኖር እንዳይደክመን።

#H
@hiwotlife
55 viewsĤå ŵĩ , 07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 10:50:29 እንባ እና ዝምታ
ድምፅ የሌላቸው
ፈጣሪ ብቻ የሚያዳምጣቸው
ቋንቋዎች ናቸው።

@hiwotlife
52 viewsĤå ŵĩ , 07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 10:50:06 (አሳዛኝ ታሪክ)

አንዲት ሴት ለፍቅረኛዋ ያለእሷ አንድ ቀን እንዲኖር challenge ትጠይቀዋለች፣ ምንም ሳያወሩ ሳይገናኙ ቀኑን ካሳለፈ ለዘላለም እንደምታፈቅረው ትነግረዋለች እሱም ይስማማል።

በቀጣዩ ቀን ፍቅረኛዋ ቀኑን ሙሉ መልእክት ሳይልክ ሳይደውል ዋለ ግን ያላወቀው ነገር ቢኖር ፍቅረኛው በካንሰር በሽታ ምክንያት ለመሞት 24 ሰአታት ብቻ ነበር የቀራት
በቀጣዩ ቀን ልጁ ወደፍቅረኛው ቤት ሄደ
"አደረኩት የኔ ፍቅር " አለ ግን ከመቀፅበት ከአይኖቹ የእንባ ዘለላዎች ወረዱ ምክንያቱም ፍቅረኛው በሬሳ ሳጥን ውስጥ ነበረች ለመጨረሻ ጊዜ የፃፈችለት ደብዳቤ ይህ ነበር....." አደረከው ፍቅሬ በል አሁን ሁልቀን አድርገው እሺ እወድሀለው"

@hiwotlife

ታሪኩ እንዴት ነበር?
48 viewsĤå ŵĩ , 07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 06:35:30 ለመስነፍ አልተፈጠርክም!

የመጀመሪያው ጠንክሮ የመስራት ሸክም ነው፤ ሁለተኛው የፀፀት ሸክም ነው። ጠንክሮ መስራት ምናልባት 1 ኪሎ ግራም ቢመዝን ነው፤ ፀፀት ግን 100 ኪሎ ግራም ተሸክሞ እንደመዞር ነው። የቱ እንደሚሻልህ አንተው ምረጥ!

ሁላችንም አሁን ካለንበት የተሻለ ነገር እንፈልጋለን፤ በከንቱ ቀንህ ያለፈ ጊዜ "በቃ አይኔ እያየ ምንም ሳልሰራበት ቀኑ አለፈ?" እያልክ ራስህን የወቀስክበትን ጊዜ አስብ፤ አየህ ወዳጄ ጠንክረህ የምትሰራው ከፍ እንድትል ብቻ አይደለም ሁሌም ከራስህ ጋር እንድትስማማ ነው።

ግሩም ሰኞ
@hiwotlife
45 viewsmeski , 03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 15:44:06 የብርሃን አመት (Light year)
-------------------
የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች እንደሚያስቀምጡት ከመሬት ወይም ከምድራችን ውጪ ሆነን አይናችን እስከፈቀደልን ድረስ እና በግዙፍ ቴሌስኮፖች ታግዘን የምናየውን የዩኒቨርስ ጥግ የሚታየው ዩኒቨርስ ወይም (Observable universe) ብለን እንጠራዋለን። የማጉላት አቅማቸው እጅግ ከፍተኛ የሆኑት እንደ ሀብል ያሉ ቴሌስኮፖች በዩኒቨርስ ውስጥ ስላሉት ነገሮች የሚያዩት እስከተወሰነ ርቀት ብቻ ነው። ምድራችን ላይ የምንጠቀማቸው የርዝመት መለኪያ መስፈርቶች ወደ ህዋ ስንወስዳቸው የቅንጣት ቅንጣት ናቸው።
የህዋ አካላት የሚራራቁበት የርዝመት መጠን በሜትሮችም ሆነ በኪሎሜትሮች ብንለካው አጅግ በጣም ግዙፍ ቁጥር ነው። ስለዚህ ሌላ የርዝመት መለኪያ መስፈርቶች በማስፈለጋቸው የኮስሞሎጂና የፊዚክስ ሊቃውንት የብርሀን አመት ወይም (Light year) የህዋ ውስጥ ርቀት መለኪያ እንዲሆን ወሰኑ። የብርሀን አመት የጊዜ ሳይሆን የርዝመት መለኪያ ነው። አንድ የብርሀን አመት ብርሀን በአንድ አመት ውስጥ የሚጓዘው የርቀት መጠን ነው።
ብርሀን በአንድ ሴኮንድ ውስጥ 300,000 ኪ.ሜ የሚጓዝ ሲሆን ይህ ርቀት ወደአመት ሲጠጋጋ 9 ትሪሊዩን ኪሎሜትሮች ይሆናል። በመሆኑም አንድ የብርሀን አመት ሲባል 9 ትሪሊዩን ኪ.ሜ ለማለት ነው።
በዚህ ስሌት ከላይ እንደተጠቀሰው የሚታየው ዩኒቨርስ 93 ቢልዩን የብርሀን አመት ይረዝማል ስንል ለአገላለፅ ቀለለ እንጂ በመጠነ ግዘፍት ሲሰላ ከሰው ልጅ የማሰብ አቅም በላይ እንደሚሆን የሚታወቅ ነው። በቅርበት ደረጃ እንኳን ለኛ ቅርብ የሆነችዋ 'ፕሮክሲመስ ሴንታውሪስ' የተሰኘችዋ ኮከብ 4 የብርሀን አመታት ርቃ ነው የምትገኘው። ያለንበት ሚልኪ ዌይ ጋላክሲ ከጥግ እስከ ጥግ 100,000 የብርሀን አመታት ይረዝማል። ለኛ ቅርብ የሆነው አንድሮሜዳ ረጨት ደግሞ 2.5 ሚልዩን የብርሀን አመታት ርቆ ይገኛል።
ምንጭ፡ Airtable universe

@hiwotlife
@hiwotlife
@hiwotlife
54 viewsBiruk Muleta, edited  12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 15:35:16 ወዛደር እና ወዝውዞ አደር
(በእውቀቱ ስዩም)
በቀደም አንድ የተባረከ ዜጋ “የዶሮ በሽታ ገብቷል” ሚል ወሬ ነዝቶ የእንቁላልን ዋጋ ቁልቁል ወሰደው፤ አጋጣሚውን ለመጠቀም ሞከርኩ፤ የቤት ሰራተኛየ “ዛሬ ምን ይሰራልህ?” ስትለኝ “ ቆንጆ ሽሮ አንተክትኪልኝና አንድ አምስት የተቀቀለ እንቁላል ጣል አርጊበት” እላታለሁ፤ ከጥቂት ቀናት በሁዋላ የሆነ ክሊኒክ ምርመራ አደረግሁ፤ ኮሌስትሮል ውጤቴን ሲመለከቱ፥ ዶክተሮችና ነርሶች ተሰብስበው ተላቀሱ ፤ የክሊኒኩ ዘበኛ ግን “ አይዞህ ! በርሀብ ሞተ ከምትባል በኮሌስትሮል ብዛት ሞተ ብትባል ለስምህ ጥሩ ነው “ በማለት አጽናናኝ ::
በማግስቱ እዚህ ሀያ ሁለት ማዞርያ -ቺቺኒያ በሚገኘው ጂም ቤት Fitness dancing ተመዘገብኩና መስራት ጀመርኩ፤
“ ምንድነው እምታደርጉት?” አለኝ ምኡዝ ፤ መስራት መጀመሬን የነገርኩት ቀን፥
“በጋራ እንወዛወዛለን፤ እንደንሳለን፤ “
“ አላማው?”
“ክብደት ለመቀነስ ይጠቅማል”
ምኡዝ መሳቅ ጀመረ፤
“ምን ያስቅሀል?”
“ በውዝዋዜ መክሳት ቢቻል ኖሮ ፥ ሰማኸኝ በለው ይከሳ ነበር ‘
“ ተው! ተስፋ አታስቆርጠኝ”
“ በውዝዋዜው ቀጥል! የወረቀት ዋጋ ስለተወደደ ከዚህ በሁዋላ በደራሲነት መኖር ይከብዳል፤ ስለዚህ ተጠባባቂ ሙያ ይዞ መገኘትህን አልጠላሁትም”
በሀሳቤ ፥ በቅርቡ ሀገር ፍቅር ትያትር የቅጥር ቃለመጠይቅ ሳደርግ ታየኝ፥
ቃለመጠይቅ አድራጊው " የውዝዋዜ ልምድ አለህ?’ሲለኝ፥የሚከተለውን እምነግረው ይመስለኛል፤
ድሮ ጎረምሳ እያለሁ ባልተጠራሁበት ሰርግ የመታደም ልምድ ነበረኝ ፤ ተበልቶ ተጠጥቶ ሲያበቃ” እስቲ አምጣው የደሙን ሸማ” እሚል ዘፈን አየሩን ይሞላዋል፤ እንግጣ (ጭፈራ) ይጀመራል፤ ሴቶች ጠልሰሙና ድሪው ደረታቸው ላይ እስኪነጥር ድረስ ይንቀጠቀጣሉ፤ ወንዶች ይወረገረጋሉ፤
ድንገት “ ያ ልጅ መጣ! በውቄ መጣ” ይባላል፤ እስክታ መቺዎች እስክስታውን አቁመው አንገታቸውን ደፋ አድርገው ማጨብጨብ ይጀምራሉ፤ ባልቴቶች “ ሰፋ አርጉለት “ እያሉ መለፈፍ ይጀምራሉ፤ አረጋውያኑ በበኩላቸው” አየየ! ዳሱን ካላፈረስንለት በቀር አስፍተን አንችለውም” ብለው ይተክዛሉ፤ እጀምራለሁ፤ እርግፍ እርግፍ እላለሁ፤ ክንዴ ባይብሬተር ሞድ ላይ እንዳለ ኖኪያ ሞባይል ሳያቁዋርጥ ይንቀጠቀጣል ፤ ደረቴ እንደ እፉየ ገላ ይገላበጣል ፤መላው ዳሞት፥ ድፍን ጎጃም “ በውኑ ይሄ ልጅ አጥንት አለውን” በማለት ይደነቃል፤ ወድያው ካጥንትም፥ ብርቱ አጥንት እንዳለኝ ማረጋገጥ የፈለግሁ ይመስል በእግሬ ወለሉን መደለቅ እጀምራለሁ፤ እንዲያውም፥ የሆነ ጊዜ ላይ መሬቱን በሀይል ደጋግሜ ከመደለቄ የተነሳ ውሀ ፈለቀ፤ በውሀው እንዳትሌት ፊቴን አረጣጥቤ እስክስታውን ቀጠልኩ፤
ቃለመጠይቅ አድራጊው አድምጦኝ ሲያበቃ፤-
“ ወደ ቤትህ መሄድ ትችላለህ! በቀደዳ ዘርፍ ክፍት የስራ ማስታወቂያ ስናወጣ እንጠራሀለን”

@hiwotlife
@hiwotlife
@hiwotlife
50 viewsBiruk Muleta, 12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 07:43:01 አንዳንዴ ብዙ ብዙ መናገር እኔነቴን መግለፅ የሚችል ይመስለኛል አንዳንዴ ዝም ማለት እኔን ለማስረዳት በቂ ይመስለኛል ወይም ሁለቱንም መሆን አንዳንዴ ዝም አንዳንዴ መናገር ብቻ አላውቅም

@hiwotlife
57 viewsĤå ŵĩ , 04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 07:41:48 ....

. . .​​​​ሴት ልጅ ብዙ ነገር ልትዋሽ ትችል ይሆናል!የውሸትዋን ግን በፍፁም እወድሀለሁ አትልህም! ወንድ ልጅ ለፍቅሩ መስዋት ከመክፈሉ በፊት ስለ ብዙ ነገር ያስባል በዙሪያው ስላሉ ሰዎች፣ስለ ስራው ፣ስለ ቤተሰቦቹ ወዘተ...
ሴት ልጅ ስታፈቅር ግን ስለ ነብስዋ ይሆን ስለምንም ነገር ማሰብ አቁማ ሁሉን ነገር ረስታ ስለአንተ ስለ ፍቅርዋ ማሰብ ትጀምራለች!

@hiwotlife
57 viewsĤå ŵĩ , 04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 07:40:44 አላወራም

ስላንተ ፍቅር አላወራም። ስለፍቅርህ አላልኩም አልያም ስለአንተነትህ ግን ህይወቴ እኔ አላወራም። ስንት ግዜያትን ይሁን በሲቃ እንባ ያስለቀስከኝ? ስንት ግዜያትንስ ነው በደስታ እንባ ያጠብቀኝ?? በመከፋቴ ይሁን በደስታህ ውስጥ እንዳገኘሁህ ባላውቅም ግን ሀሴቴ ነህ። የኔ ጌታ የምልህ ከማስብልህ ያንስብኝና ምንም እንዳልል ያስገድደኛል። አዎ ፍቅሬ ስለእኛ ብለን ስለእኛ በሚሆነው ምንም ነገር አላወራም።

ህይወቴ በፍቅርህ ጠፍቻለሁ፤ ዳግም እንዳይታየኝ ታውሬልሀለሁ። ለዛም ነው መሰለኝ ብዙ እያለምኩኝ ዝምታን የመረጥኩት ግን ስለ ስሜቴም ልነግርህ አልፈልግም። ኧረ በፍፁም አላወራምም። አንተ አንተ እኔነቴ ነህ የመከፋቴ ምትክ የኔ ፍቅር ከራስ በላይ ከምታፈቅረኝ በላይ እኔ አፈቅርሀለሁ።



join us
@hiwotlife
54 viewsĤå ŵĩ , 04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 07:38:28 ሰርቄ ሳይህ
የአይንህ የብርሀን ወገግታ
የከንፈርህ እንቅስቃሴየትንፋሽህ ስልምልምታ
የድምፅ ልስላሴ የአወራርህ እርጋታ
የአረማመድህ ስክነት
የክንዶችህ ሙቀት
የጣቶችህ ማማር ሎጋነት
የቁመናህ ርዝመት
የጥርስህም ንጣት
ታወሰኝ ገና አሁን ስደርስ እቤት
አንተ ሳታየኝ ሰርቴ ያየዉህ እለት

@hiwotlife
52 viewsĤå ŵĩ , 04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ