Get Mystery Box with random crypto!

የብርሃን አመት (Light year) ------------------- የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች እንደ | 🦋Ľĭ£€🦋

የብርሃን አመት (Light year)
-------------------
የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች እንደሚያስቀምጡት ከመሬት ወይም ከምድራችን ውጪ ሆነን አይናችን እስከፈቀደልን ድረስ እና በግዙፍ ቴሌስኮፖች ታግዘን የምናየውን የዩኒቨርስ ጥግ የሚታየው ዩኒቨርስ ወይም (Observable universe) ብለን እንጠራዋለን። የማጉላት አቅማቸው እጅግ ከፍተኛ የሆኑት እንደ ሀብል ያሉ ቴሌስኮፖች በዩኒቨርስ ውስጥ ስላሉት ነገሮች የሚያዩት እስከተወሰነ ርቀት ብቻ ነው። ምድራችን ላይ የምንጠቀማቸው የርዝመት መለኪያ መስፈርቶች ወደ ህዋ ስንወስዳቸው የቅንጣት ቅንጣት ናቸው።
የህዋ አካላት የሚራራቁበት የርዝመት መጠን በሜትሮችም ሆነ በኪሎሜትሮች ብንለካው አጅግ በጣም ግዙፍ ቁጥር ነው። ስለዚህ ሌላ የርዝመት መለኪያ መስፈርቶች በማስፈለጋቸው የኮስሞሎጂና የፊዚክስ ሊቃውንት የብርሀን አመት ወይም (Light year) የህዋ ውስጥ ርቀት መለኪያ እንዲሆን ወሰኑ። የብርሀን አመት የጊዜ ሳይሆን የርዝመት መለኪያ ነው። አንድ የብርሀን አመት ብርሀን በአንድ አመት ውስጥ የሚጓዘው የርቀት መጠን ነው።
ብርሀን በአንድ ሴኮንድ ውስጥ 300,000 ኪ.ሜ የሚጓዝ ሲሆን ይህ ርቀት ወደአመት ሲጠጋጋ 9 ትሪሊዩን ኪሎሜትሮች ይሆናል። በመሆኑም አንድ የብርሀን አመት ሲባል 9 ትሪሊዩን ኪ.ሜ ለማለት ነው።
በዚህ ስሌት ከላይ እንደተጠቀሰው የሚታየው ዩኒቨርስ 93 ቢልዩን የብርሀን አመት ይረዝማል ስንል ለአገላለፅ ቀለለ እንጂ በመጠነ ግዘፍት ሲሰላ ከሰው ልጅ የማሰብ አቅም በላይ እንደሚሆን የሚታወቅ ነው። በቅርበት ደረጃ እንኳን ለኛ ቅርብ የሆነችዋ 'ፕሮክሲመስ ሴንታውሪስ' የተሰኘችዋ ኮከብ 4 የብርሀን አመታት ርቃ ነው የምትገኘው። ያለንበት ሚልኪ ዌይ ጋላክሲ ከጥግ እስከ ጥግ 100,000 የብርሀን አመታት ይረዝማል። ለኛ ቅርብ የሆነው አንድሮሜዳ ረጨት ደግሞ 2.5 ሚልዩን የብርሀን አመታት ርቆ ይገኛል።
ምንጭ፡ Airtable universe

@hiwotlife
@hiwotlife
@hiwotlife