Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል 5 የትናንሽ ልጆች ጠብና ግብግብ ውስጥ የተወሰኑ ፋይዳዎች አሉት። -ሌሎችን ለማሸነፍ አቅ | ሂላል ኪድስ Hilal Kids

ክፍል 5

የትናንሽ ልጆች ጠብና ግብግብ ውስጥ የተወሰኑ ፋይዳዎች አሉት።
-ሌሎችን ለማሸነፍ አቅም ያላቸው መሆኑን ያውቁበታል፡፡
-ይቅርታን፣ ድል አድራጊነትና (አሸናፊነትን)፣ ሽንፈትን የመቀበል ልምድን ያዳብሩበታል።
-እንደዚሁም ደካማ ጎናቸውንም ይለዩበታል፡፡
-ጠቡ ቀላልና በስሱ ከሆነ ከቤቱ ድብርትን ለማባረር መተራረብና ደስታን ለቤቱ ሊለግሱት ይችላሉ -በጠቡ መሃል በሚገኙ አጋጣሚዎች ለመዝናናትም ይቻል ይሆናል፡፡

ቤት ለልጆች የተለያዩ የህይወት ተሞክሮዎችን የሚለማመዱበት የመሰልጠኛ ማዕከል መሆኑም መዘንጋት የለበትም፡፡
በመሆኑም አንድ ቤት በልጆች መካከል ምንም አይነት ሽኩቻ (ጠብና ንትርክ) የሌለበት መሆኑ አዎንታዊ መልእክት አስተላላፊ አይደለም፡፡

#የልጆች ጠብ ችግር የሚሆነው መቼ ነው?

በልጆቻችን መሀከል የሚኖረው ጠብና ንትርክ አሳሳቢና አስፈሪ የሚሆነው ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት ሁኔታዎች ይፋ መሆን የጀመሩ እንደሆነ ነው
1. የቃላት ልዩነት (ንትርኩ) ወደ ቦክስ መሰናዘር እና ከባድ ቁጣን የወለደ ከሆነ ወይም ዱላ መማዘዝ በማስከተል በአንደኛው ወገን ላይ የአካል ጉዳት የሚያደርስ ድብድብ ከተሸጋገረ

2. በጠቡ መካከል አስቀያሚ ቃላትን መጠቀም ከጀመሩ

3. ባልተለመደ ሁኔታ ተደጋጋሚ ጠብ ውስጥ መግባታቸው ከታየ

4. ቤተሰቡን ወደ መረበሽና የት/ት ሒደታቸው ላይም ተፅዕኖ ማሳረፍ ከጀመረ

5. በወንድሙ እንደተሸነፈና፣ በደል እንደተፈጸመበት የሚሰማው ወገን መገኘት በተለይ በታላቁ ግፍ ተፈፅሞብኛል ብሎ ታናሽ መብሰልሰል ከጀመረ

አንደኛው ልጅ ዘንድ የብቀላ ስሜት (መንፈስ) እየጎለበተ መምጣቱን ካስተዋልን ጉዳዩ ገደቡን አልፎ ሌላ መዘዝ ከማምጣቱ በፊት የቤተሰቡ ጣልቃ ገብቶ ነገሮችን ለማስተካከል መሞከር የግድ አስፈላጊ ይሆናል፡:

በቀጣይ ስለመንስኤዎቹና መፍትሔዎቹ ይዘን እንመለሳለን