Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል 4 በልጆች መካከል የሚከሰት ጠብ የሰው ልጅ በአጠቃላይ ልጅም ሆነ አዋቂ በብቸኝነት መኖር | ሂላል ኪድስ Hilal Kids

ክፍል 4
በልጆች መካከል የሚከሰት ጠብ

የሰው ልጅ በአጠቃላይ ልጅም ሆነ አዋቂ በብቸኝነት መኖር የማይችልና ማህበራዊነትም መገለጫው የሆነ ፍጡር ነው፡፡ ነገር ግን የበርካቶች መሰባሰብና አብሮነት ለተለያዩ የውድድር መንፈሶች መዳረጉ የታወቀ እውነታ ነው ከዚያም አልፎ ክርክር ፣አለመግባባት፣ንትርክና በአጠቃላይ የመልካም ግንኙነት መበላሸት መከሰቱ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው፡፡ የዚህ ጉዳይ መሰረታዊ መነሻው ደግሞ በሰዎች መካከል ያለና የሚኖረው የሃሳብ፣ የፍላጎት (ዝንባሌ)፣የአስተዳደግ፤ የጥቅም፣ነገሮችን የምንመለከትበት መነፅር መለያየት ነው፡፡ አንድ ግልፅ መርህ ቢኖር እያንዳንዱ ግለሰብ ለሌላ ግለሰብ ሌላ ሰው የመሆኑ ሚስጥር ነው፡፡ እናም ያ ሰው በዚህኛው ላይ የተለያዩ ምቾቶችን የሚነፍጉ ድርጊቶች በተለያዩ አጋጣሚዎች ሊፈፀምበት ይችላል፡፡ ስለሆነም የማናችንም ቤት ከመጎናተልና ከመጎሻሸም እንደምን ሊወገድ ይችላል። ከላይ የጠቀስናቸው የተለያየ ስብዕና የተበላሱ ሰዎች በአንድ ጣራ ስር ሲኖሩ መነካካት የሚጠበቅ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የተለመደና ከቁጥጥር ውጭ የማይሆነው ንትርክና ከተለመደው ወጣ የሚል እንዲሁም አሳሳቢና አደገኛ የሆነም አይነት አለ፡፡

#በርካታ ጥናቶች እንዳመላከቱት በወንድማማቾች (እህትማማቾች) መካከል የሚኖር እሰጥ አገባ ከእድሜ መጨመር ጋር እየቀነሰ የሚመጣ ክስተት ነው ለምሳሌ የ 8 ዓመት ህፃናት (ልጆች) ከ 4 ዓመት ህፃናት ያነሰ ጠብ ውስጥ የመግባት አጋጣሚ አላቸው፡፡

በተመሳሳይ ጾታዎች መካከል ፀበኝነቱ እንደሚበረታም ምሁራኑ አመላክተዋል፡፡
ተቀራራቢ እድሜ ባላቸው ለምሳሌ 5 እና 6 ወይ ከ1 ዓመት ወይም ከዓመት ተኩል እስከ 2 ዓመት ልዩነት ባለበት ትግሉ ይበረታል።
እዚህ ጋር ሊነሳ የሚገባው ነጥብ ግን የትናንሽ ልጆች ጠብና ግብግብ ውስጥ የተወሰኑ ፋይዳዎች ያሉት መሆኑን ነው፡፡

እነዚህ ፋይዳዎች ምን ምን ናቸው የሚለውን በቀጣይ ይዘን እንመለሳለን በአላህ ፍቃድ