Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል ሁለት #ውሸትን ከልጆቻችን ላይ እንዴት ማስወገድ እንችላለን? እድሜያቸው አራትና አምስት | ሂላል ኪድስ Hilal Kids

ክፍል ሁለት

#ውሸትን ከልጆቻችን ላይ እንዴት ማስወገድ እንችላለን?

እድሜያቸው አራትና አምስት አመት አካባቢ የሆኑ ልጆች ውሸት መናገራቸው ብዙ አያስጨንቅም፡ ምክንያቱም እነዚህ ልጆች በዚህ እድሜያቸው የገሃዱን እና የምናቡን አለም ልዩነት ብዙ አይረዱትም፡ የሚናገሩት ከተጨባጩ አለም ጋር ይሄዳል አይሄድም ብሎ ለመመዘን የሚያስፈልገው ክህሎት ገና አልዳበረላቸውም፡፡

ልጆችህን ጠባብ ክፍል ውስጥ ወስደህ የወንጀል ምርመራ ስራ አትስራ ማለትም ይህን ይህን ሰርተሃል እመን እያልክ አታስፋራራ፡ ማስረጃ ባጣህለት ነገር እራሱ ላይ መስክሮ እንዲቀጣልህ አትፈልግ (ጥፋት አጥፍቶ ሊሆን ይችላል ግና በዚህ መንገድ ለማሳመን መሞከርህ ውጤታማ አይደለም)፡፡

#ልጆቻችን ላይ ውሸትን ለማስወገድ የሚረዱን መንገዶች

❖ ልጆቻችን በራሳቸው እንዲተማመኑና ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን የኑሮ ሁኔታ አምነው እንዲቀበሉ ማድረግ፡-

አንዳንድ ጊዜ ህጻናት ለራሳቸው ክብርን ወይም የሆነ የጎዳላቸውን ነገር ለመሙላት ብለው ሲዋሹ ይገኛሉ ይህን የሚያደርጉት ያለባቸውን የዝቅተኝነት ስሜት ለማጥፋት እና እኔ ትልቅ ነኝ ጠቃሚ ሰው ነኝ የሚል መንፈስን ለመላበስ ነው፡ ለምሳሌ ብዙ ህጻናት አባቶቻቸው ሃብታም እንደሆኑ ለማሳወቅ ውድ ነው ብለው የሚያስቡትን ንብረት አለን ይላሉ፡ ይህ ቤታቸው ውስጥ ያለውን ድህነት ለመደበቅና ድሃ ነን የሚለውን ስሜት ለማስወገድ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው፡፡

❖ ቤት ውስጥ እውነትን ብቻ መናገር እና ስለ እውነት መሞገት፡-

አባት እናትን፤ታላቅ ወንድም ታናናሾቹን፤ሴቶቹ ጓደኞቻቸውን በሚዋሹበት ቤት የሚያድግ ህፃን በምንም ምክንያት ውሸትን እንዲተው አይጠበቅበትም የቤቱ ባህል ሆኗልና፡፡ስለሆንም እውነትን ብቻ በመናገር ልጂ ውሸትን አነውሮ እንዲመለከት ይረዳዋል፡፡

❖ በጣም የተጋነነ ውሸት (ወላጆች ስለስራቸው ሁኔታ አጋኖ አለማውራት) ፡-

አንድ ወጣት እንዲህ ሲል ያወራል፡ እናቴ ስለአባቴ ስራ ለጓደኞቿ ስታወራ እሰማለሁ ፡ የሚሰራው እጅግ ቁልፍ የሆነ የሀገሪቱ መስሪያ ቤት ውስጥ በመሆኑ ተደጋጋሚ ፊልድ ይወጣል ትላለች፡ እኔም ት/ቤት ለማገኛቸው ጓደኞቼ እሷ ያለችውን እላቸው ነበር፡ በዚያም ሲቀኑብኝ አስተውላቸው ነበር፡ ልክ ሁለተኛ ደረጃ ስጀምር አንድ ቀን ከባድ አደጋ ወደቀብኝ አባቴ የአንድ ኢንቨስተር ተላላኪ ሆኖ ከዚያ ሰው ጋር ላይ ታች የሚል እንጂ ሌላ አለመሆኑን ስረዳ ይላል፡፡

ቀሪዎቹን መፍትሔዎች በቀጣይ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።