Get Mystery Box with random crypto!

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته #ዋና_ዋና_የህጻናት_የባህሪ_ችግሮች! ክፍል አ | ሂላል ኪድስ Hilal Kids

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

#ዋና_ዋና_የህጻናት_የባህሪ_ችግሮች!
ክፍል አንድ

=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=

ውሸት

ሕጻናት ከሚገጥማቸው ችግሮች መካከል ዋናውና የመጀመሪው ውሸት ነው፡በአሁኑ ሰዐት ውሸት ከህፃናት አልፎ በአዋቂዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እንደወረርሽኝ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ይህ የሚሆነው የሰው ልጆች ለዱንያ ያላቸው ጉጉትና ፍቅር ድንበር ሲያልፍ፤ የማህበራዊ ህይወት ምስቅልቅል መብዛት፤ በተለይም የድህነት መስፋፋትና የእለት ጉርስን ማግኘት ሲከብድ ውሸታሞችን መብዛት ብንጠብቅ አይገርምም፡እናም አንድ ህብረተሰብ እውነተኛና ትክክለኛ ስልጣኔ ለመገንባት ከፈለገ ከእውነተኛነትና ውሸታምነት ጋር ያለውን ቁርኝት ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

#ውሸት_ምንድን_ነው?

አብዛኛውን ጊዜ ውሸት የሚፈጠረው ከሆነ ወንጀል(ስህተት) ወይም ማድረግ ያለብንን ስላላደረግን ወይም የሆነ ነውርን ለመደበቅ ሲባል ነው፡፡ ይህም ማለት አንድ ሰው በፈለገው መንገድ ይሁን የሚሰራውን ሰርቶ ለመደበቅ የሚችልበትና ለሰራው ስህተት የእጁን እንዳያገኝ የሚያስቸል ግርዶ ነው፡፡እናም ውሸት ላይ መዘውተር ማለት ለሁሉም መጥፎ ስራዎች በር መክፈት እንደሆነ ይታመናል፡፡

ስለህጻናት ውሸት ስናወራ ደግሞ ልጆች አንድ ከተከሰተ ነገር በተቃራኒ ሲናገሩ ዋሹ ብለን እንላለን:: ያም እውነታውን ለመደበቅ አልያም ሌሎችን ለማሳሳት ብለው የሚናገሩት ንግግር ሲኖር ነው፡፡

#የውሸት_አደገኛነት!

በማታለልና በውሸት እንዲሁም ቅጥፈት መካከል ጠንካራ ትስስር አለ፡፡ ዛሬ በአለማችን በሚከሰቱ ወንጀሎች ዙሪያ የተደረጉ በርካታ ጥናቶች እንዳመለከቱት ውሸታሞች በአብዛኛው ሌቦችና አታላዮች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ውሸት እንደባህሪ ያለበት ሰው ማታለልና መስረቅም አብረውት የሚገኙት ባህሪያቶቹ ናቸው፡፡ እናም ይህ ጥምረት የሚገርም አይሆንም ፡ ምክንያቱም ከሃዲዎች እውነታን፤ መርህንና ቃልኪዳንን ጭምር የሚክዱ ሰዎችን ካየን ይህ ባህሪያቸው የተፈለቀቀው ከውሸታምነታቸው መሆኑን እንረዳለን፡፡

ከዚህ በመነሳት የአላህ መልእክተኛ በቃልም በተግባርም ውሸትን አጥበቀው የመታገላቸውን ሚስጥር እንረዳለን። ይህን ያደረጉት በህጻናትም በአዋቂዎችም ላይ ነበር። አብደላህ ኢብኑ አማር የሚባል ሰሃባ እንዳወራው አንድ ቀን እናቱ ጠራችውና የሆነ ነገር እሰጣሃለው አለችው፣ ነቢዩም ምንድን ልትሰጪው ነው ሲሉ እሷም ቴምር አለች፣ እሳቸውም ምንም ባትሰጪው ይህቺው ንግግርሽ ውሸት ተብላ ትመዘገብብሽ ነበር አሏት፡፡

አኢሻም (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዓ.ወ) ከቤተሰባቸው በአንዱ ላይ ውሸትን ካዩበት ያ ሰው አምኖ ተውበት እስኪያደርግ ድረስ አያናግሩትም ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ የሚያሳየን ግልጽ አቋማቸውን ነው። ውሸት ካለበት ሰው ጋር ንክኪ የላቸውም በተግባርም በኩርፊያና በመለያየት በዚያ ሰው ባህሪም ላይ ያላቸውን ግልጽ ቅሬታ በማሳየት ዳግም ወደዚህ መጥፎ ስነምግባር እንዳይመለስ በተግባር ያስተምሩ ነበር። ይህም አሳዳጊዎችና ወላጆች ልብ ሊሉት የሚገባ መልካም አርአያነት ነው፡፡

#ህጻናት_ለምን_ይዋሻሉ?

በመጀመሪያ ልብ ልንለው የሚገባ ነገር ውሸት እዚህ አለም ከመጣን በኃላ በትምህርት፤ ከሌሎች በማየትና ከህይወት ተሞክሮዎች የምናገኘው ማህበራዊ ክህሎት እንጅ በተፈጥሮ የሚወራረስ ባህሪ አለመሆኑን ነው፡፡በአንድ ቤተሰብ አባላት ውስጥ የውሸት መስፋፋት የሚጠቁመው እዚያ ቤት ወይም ማህረሰብ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ዝቅተኝነትና ዋጋ ቢስነት ነው።

በአዎንታዊ መልኩ ህጻናት በሁለት መሰረታዊ ሁኔታዎች ለውሸት ተጋልጠው ልናገኛቸው እንችላለን፦

የቋንቋ አቅማቸው፡-
የልጆች የቋንቋ አቅም የሚፈቅደውን የቃላት ብዛት በመጠቀም የሚፈልጉትን ነገር ሊናገሩ ይችላሉ። ይህም ፍላጎታቸው ከእውነታው ጋር ምን ያህል ይጣጣማል የሚል እሳቤን ላያካትት ይችላል፡፡

የምናብ ግጥምጥሞሽ መከሰት፡-
ሁኔታወችን በራሳቸው ምናብ በማገጣጠም እውነት ያልሆነን ነገር ሊናገሩ ይችላሉ፡፡
ነገር ግን በአሉታዊ አንፃር ስናየው ህጻናትን ወደ ውሸት የሚገፋፉ ዋና ዋና ምክንያቶችን እናያለን፡

1. ቅጣትን በመፍራትና የምፈልገውን ነገር እከለከላለሁ በሚል ፍርሃት መዋሸት

2. ወላጆችና አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን ለማሳመንና ያጠፉትን ጥፋት እንዲቀበሉት ለማስገደድ ጉልበትንና ቅጣትን በተገበሩት ቁጥር ልጆች እራሳቸውን ለማዳን ሲሉ መዋሸት

3. በአድማጮቻቸው ለመደነቅ ወይም ትኩረትን ለመሳብ

4. የሆነን ነገር ለማግኘት ብሎ መዋሸት (ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ሲሉ ከትምህርት ቤት አምጡ ተብለናል በማለት ገንዘብ መቀበል ሊሆን ይችላል)

5. ከራሳቸው ላይ አደጋን ለመከላከል ሲሉ እርስ በርስ ሊውሻሹ ይችላሉ

6. ከወላጆች በመቅዳት የነሱን ባህሪ መያዝ፡- የሚዋሹ ህጻናት ብዙውን ጊዜ የሚዋሹ አባቶቻቸውን ወይም እናት ወይም ታላላቅ እህትና ወንድሞቻቸውን ኮፒ አድርገው እናገኛቸዋለን፡ አንድ ወጣት ይህን አስመልክቶ ሲናገር አባቴ ሲሰራና ሲናገር የማየው ነገር በሙሉ ትክክልና እውነት ይመስለኝ ነበር፡ ውሸትን የተማርኩት ከአባቴና እናቴ ነው፡፡በአንድ ወቅት እኔ እንድተኛ ብለው እነሱ እንደተኙ ያስመስላሉ ከዚያ ስተኛ ተነስተው የሚሄዱበት ይሄዳሉ አንዴ እናቴ እንዲህ አለችኝ ይላል ተነስ መጫወቻ ቦታ ልውሰድህ ብላ በጣም ደስ ብሎኝ እየሄድን ስንደርስ እራሴን የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ወንበር ላይ አገኘሁት ይላል፡፡

=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=

በቀጣይ ልጆቻችን ላይ ውሸትን እንዴት ማስወገድ እንችላለን የሚለውን እናያለን በአላህ ፍቃድ፡፡