2022-02-09 12:35:58
#ድንቆች አለማቸው ሌላ ነው!
ደንቆች አለማቸው ሌላ ነው፤
አላማቸው ከፍ ይላል፤ የተለዩ ናቸው፣ የተለየ ነገር ስለሚያደርጉ። ስኬት በእጃቸው ነው፤
ሰርቀው ሳይሆን ሰርተው ያመጡታል፤
አዋርደው ሳይሆን ተዋርደው ያመጡታል፤
ከእግር በታች ወድቀው፣ ዝቅ ብለው ከፍታው ላይ ይደርሳሉ፤
ትኩረታቸው ተግባራቸው ላይ ነው፤ ድርጊታቸው የስኬት ጥማታቸውን ያሳያል፤ የተሻለ ህይወት እንደተራቡ ያመለክታል።
ህይወትህ አልሰለቸህም? ለውጥ የሌለው ህይወት፣ ፈቀቅ የማይል፣ ክፍ የማይል ተመሳሳይ አሰልቺ ህይወት እንዴት አይሰለችህም? በምንም ተዓምር ሊመችህ አይችልም። እና ማንን እየጠበክ ነው?
ማነው ከዚህ አሰልቺ ህይወት የሚያወጣህ?
ማንም አይመጣም! በፍፁም እንዳታስበው፤ ከአዕምሮህ ጠራርጎ አስወጣው።
መንግስት ደሞዝህን እስኪጨምር እየጠበክ ነው?
ፍቅረኛህ መልዕክትህን እስክትመለስ እየጠበክ ነው?
ህልምህን ሌላ ሰው እንዲነግርህ ትመኛለህ?
ችግርህን እንዲፈታ ሌላ ሰው ታስባለህ?
በፍፁም እንዳታስበው! ሌላው ያንቀላፉ እንደሆነ አንተ በጭራሽ እንዳታንቀላፋ፤ ን..ቃ! ዙሪያህን ተመልከት፤ ምን እየተከናወነ ነው?
ማን ምን እያደረገ ነው?
ሰነፎች የት ናቸው?
ብርቱዎችስ የት ደርሰዋል?
እንዴት ደረሱ? መርምር! አመዛዝን! እራስህን አስተካክል።
አዎ! በኩራት የድንቆቹን አለም ተቀላቀል።
ሃላፊነት ከሚሰማቸው፣ አሳንሰሩን ሳይሆን ደረጃውን ከተጠቀሙት፣
ለምድር ሸክም ከሆኑት ሳይሆን ምድርን ከሚሸከሙት፤
ህልማቸውን በማንኮራፋት ከሚያደምቁት ሳይሆን ተነስተው በተግባር ከሚኖሩት፣
ሌሊት አይተው ጠዓት ከሚጠፋባቸው የሌት ህልመኞች ሳይሆን ቀኑን ሙሉ ከሚያልሙት፣ ከሚታገሉለት ብርቱዎች ጎራ ተቀላቀል።
ምናልባት ህልም አየሁ ሊሉህ ይችላሉ፤ ህልም አለኝ ግን አይሉህም፤ ቢነግሩህ እንኳን ያላለቀ፣ ፍቺ የሌለው፣ እውን የማያደርጉትን ህልም ይሆናል። አትስማቸው! የማይኖሩትን ህልም ከሚተርኩልህ የሌት ህልመኞች ዞር በል፤ እራስህን አግልል፤ ከቀን ህልመኞች፣ ከእቅድ ባለቤቶች፣ ከአላማ ሰዎች፣ ከድንቆች ጎራ ተቀላቀል። ድንቅን እያደረክ ድንቅ አለም ፍጠር።
ውብ ቀን ይሁንልን!
@hager_beqeli
1.5K views09:35