Get Mystery Box with random crypto!

# አንድ የፈረንሳይ ተወላጅ የሆኑ አንዲት ሴት ወይዘሮ በባቡር ጉዞ ላይ ሳሉ አጠገባቸው ባለው ወን | ሀገር በቀል

# አንድ የፈረንሳይ ተወላጅ የሆኑ አንዲት ሴት ወይዘሮ በባቡር ጉዞ ላይ ሳሉ አጠገባቸው ባለው ወንበር ላይ የተቀመጠ ሻንጣ ስለነበር አንድ ሰራተኛ መጥቶ " ይህ ወንበር ለሰው መቀመጫ እንጂ ለዕቃ ማስቀመጫ አልተፈቀደምና እባክዎ ያንሡ!" ሲላቸው "አላነሳም!" አሉት::"ቢያነሱ ይሻሎታል እምቢ ካሉ ሌላ ነገር ይከተሎታል::" አላቸው:: እሳቸው ግን አላነሳም! እንዳሉ ጸኑ:: እርሱም "ያነሳሉ ያነሳሉ! ::እምቢ እያሉ ስለሆነ ላለቃዮ ልናገርና የሚደረገውን እናደርጋለን!" ቢላቸውም "ሂድ ንገር አላነሳም" አሉት:: ለአለቅየውም ተነግሮት አለቅየው መጥቶ "ያንሡ እንጂ ማንሳት አለቧት እኳ ?" ሲላቸው "አላነሳም!" በሚለው ሃሳባቸው ጸንተው የማይበገሩ ሆኑበት::በመጨረሻም ለዋናው ሃላፊ ተነግሮት ይመጥና "ይህን ሻንጣ ያንሱ" ሲላቸው "አላነሳም" አሉት:: ዋና ሃላፊውም " ለምን?" ሲላቸው "ገና አሁን አዋቂ ሰው መጣ:: እኔን የቸገረኝ እኮ እስካሁን "ለምን?" ብሎ የጠየቀኝ ሰው ባለመኖሩ ነው:: አንተ "ለምን?" ስላልከኝ አመሰግንሃለሁ!:: በመሰረቱ ሻንጣው የኔ አይደለም::"ሲሉት በመደነቅ ይቅርታ ጠየቃቸው::
@hager_beqeli