Get Mystery Box with random crypto!

#ስኬት፣ በአሸናፊነት ይገነባል! ስኬት የትናንሽ አሸናፊነት ውጤት ነው። ስኬታችን በየቀኑ በምናሸ | ሀገር በቀል

#ስኬት፣ በአሸናፊነት ይገነባል!

ስኬት የትናንሽ አሸናፊነት ውጤት ነው።
ስኬታችን በየቀኑ በምናሸንፋቸው ሁነቶች ይመሰረታል፤
ስኬታችን በጥቃቅን ነገር ላይ በምንቀዳጀው ድል ስር እየሰደደ ከፍ እያለ ይመጣል፤
አንዳንዴ ባላሰብነው መንገድ ነገሮች ሲገጣጠሙልን፣ ሲሳኩልን እናያለን።
ነገር ግን የእኛ በጥልቀት አለማሰብ ካልሆነ በቀር ሁሌም በመጣንባቸው መንገዶች ያላስተዋልነውን አሸናፊነት በእየእለቱ ተጎናፅፈናል።
የአለማችን ትልቁ ህንፃ 828ሜትር ቁመት ያለው ቡርጂ ከሊፍ የ163 የተከፋፈሉ ወለሎች ስብጥር፣ ውህድ ነው። ወለሎቹ ሲከፋፋሉ ትልቅ ባይሆኑም በአንድነት የአለማችንን ትልቁን ህንፃ ፈጥረዋል።
የየቀን ጥቃቅን አሸናፊነትታችንም አንድላይ ለላቀው ስኬት ያደርሱናል፤
በእየለቱ የምናዳብረው ተሞክሮ ወደ ከፍታው ያመራናል።
የአለማችን ትላልቅ የስኬት ተምሳሌት የሚባሉ ሰዎች ከስኬታቸው በፊት የገጠማቸውን ፈተና ስለማሸነፋቸው ይተርካሉ።
ስኬት በአሸናፊነት ይገነባል፤
አሸናፊነት፣ ከመንፈስ ጥንካሬ ይመጣል፤
የመንፈስ ጥንካሬ፣ ከበሳል አስተሳሰብ ይመነጫል፤
በሳል አስተሳሰብ፣ ከአስተዋይ ማንነት ይመጣል፤
አስተዋይ ማንነት ከቀና አመለካከት፣ ከአዎንታዊነት ይገኛል።
ቀናነት፣ ረጅም መንገድ ያስጉዛል፤
አውንታዊነት፣ የላቀ ስብዕናን ይገነባል፤
ቀና አዕምሮ፣ ችግር ለእርሱ ችግር አይደለም፤ መማሪያው፤ መንገዱ ነው።
አውንታዊ ሰው በጎን ያያል፣ መልካሙን ያገኛል፤ ቸርም ይቸረዋል።
የመልካምነት ዳርቻውም እንዲሁ መደሰት፣ ሃሴት ማድረግ፣ መንፈሳዊ እርካታን ማግኘት፤ የላቀው መዳረሻ ላይ መድረስ ነው።
ስኬትን በአሸናፊነት እንገንባ!
አሸናፊነትን በቆራጥነት እንላበስ!


@hager_beqeli