Get Mystery Box with random crypto!

ከዛስ እንዳትሉ (አስታወሰኝ ረጋሳ) … ከርቤ ብትታጠን ድኝ ብትታጠን ከላዩዋ አልጠፋ አለ የርኩሰት | ግጥም ከገጣሚያን

ከዛስ እንዳትሉ
(አስታወሰኝ ረጋሳ)

ከርቤ ብትታጠን ድኝ ብትታጠን
ከላዩዋ አልጠፋ አለ
የርኩሰት ታሪኳ የክፋቷ መጠን

እኔም ሞኛሞኙ
ምን እንዳስነካችኝ ጠንቅቄ ባላቅም
ጭራዋ ሆኛለሁ
በየሄደችበት ከሷ አልላቀቅም

(አሁን በቀደም ለት)
በተኛሁበት ላይ ወዳልጋዬ መጣች
ከዛስ አትሉኝም
ከዛማ ቦኋላ ካልጋዬ ጫፍ ወጣች

ከዛስ አትሉኝም

ከዛማ በኋላ
እጇን ገላዬ ላይ ስታርመሰምሰው
እስቲ ጉዷን ልየው
በማለት ዝም አልኳት እንዳንቀላፋ ሰው

መጀመሪያ እግሬን
ከዛም ወደላይ ከፍ
ምን ፈልጋ ይሆን
ምነካት እቺ እንከፍ
ብዬ ሳሰላስል ከራሴ ስሟገት
ሲመዘዝ አየሁት
ሊስም አሞጥሙጦ አፏ ወደኔ አንገት

አንድም ቃል ሳይወጣኝ ሳልደነባበር
ጉዷን ልየው ብዬ ዝም እንዳልኩኝ ነበር
(ከዛስ አትሉኝም)

ከዛማ በኋላ
አንገቴን
ግንባሬን
ጉንጬ ላይ
ከንፈሬን
ደረቴን
እንብርቴን ምናምን ምናምን

ብቻ የሆሆነ ቦታ ላይ
እጇ ድንገት ሲያርፍ እንዳይሆን አረገኝ
ምነካት እቺ ልጅ
በገዛ አልጋዬ ላይ
በማይሆን ሰአት ላይ ነገር ምትፈልገኝ!

ከዛ ደሜ ፈላ
ደሜ በጣም ሞቀ

(ከዛስ አትሉኝም)

ከዛማ በኋላ
ጉዷን ልየው ያልኩት አሳየችኝ ጉዴን
ስንት ዘመን ሙሉ
ውድ የነበርኩት ልጅ ረከስኩ ሁዳዴን

መቼም ያልጋ ነገር እንዲህ ነው አመሉ
ከዛስ እንዳትሉ።


ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39