Get Mystery Box with random crypto!

አንተዉ............ ሳቅህን አዉሰኝ እኔም ልሳቅበት ጥርስህን አዉሰኝ አንዴ ላግጥጥበት አይን | ግጥም ከገጣሚያን

አንተዉ............
ሳቅህን አዉሰኝ እኔም ልሳቅበት
ጥርስህን አዉሰኝ አንዴ ላግጥጥበት
አይንህን አዉሰኝ ሰርቄ ልይበት
እጅህን አዉሰኝ ሌላ ልዳብስበት
እግርህን አዉሰኝ ትቼህ ልሂድበት
አፍንጫህን ስጠኝ ሌላ ልልመድበት
ምላስህን ስጠኝ ጉብል ላጥምድበት
ቃላቶች አዉሰኝ አዳም ላማልበት
ጭንቅላትህን ስጠኝ ሴራ ልወቅበት
ሁሉንም አዉሰኝ አንተን ልሁንበት።
ብቻ ግን ልብህን አንተዉ ጋር ተዉልኝ
ካንተ ሌላ አፍቅሬ አንተን እንዲያስረሳኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39