Get Mystery Box with random crypto!

ጀፎረ በጉራጌ ባህል ጀፎረ/አውራ መንገድ/ልዩ ታሪክ አለው ለጉራጌ ጀፎረ ሁሉም ነገር ነው፡፡ አገ | የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

ጀፎረ

በጉራጌ ባህል ጀፎረ/አውራ መንገድ/ልዩ ታሪክ አለው ለጉራጌ ጀፎረ ሁሉም ነገር ነው፡፡ አገልግሎቱም ሁለገብ ነው፡፡

ለጉራጌ መንደሮች ትልቅ ውበት መላበስ ምክንያቱ ባህላዊ የቤት አሠራሩናአሠፋፈሩ ብቻ ሳይሆን ከዘመኑ መሀንዲስ ቅየሳ የማይተናነስ በመንደሮች መሀል ለመሀል የሚያልፈው ግርማ ሞገስ የተላበሰው ባህላዊ አውራ መንገድ ነው፡፡

በጉራጌ ታሪክ ጥንት መሬት የሚከፋፈለው በባህሉ በተመረጡ አባቶች(የዥር ዳነ) የመሬት ልኬት ዳኞች አማካኝነት ስለ ነበረ ጀፎረ ልኬት ይሰጠው የነበረ ሲሆን የጎን ስፋቱ እስከ 8 zhr or 35 ሜትር ሲሆን መስቀለኛ መንገዶች በሚያልፉበት እስከ 12 zhr or 90 ሜትር ስፋት ሲኖራቸው ርዝመቱ ግን በመሀል የሚያልፍ ወንዝ ገደል ወይም ደን እስከሌለ ሳያቋርጥ ይቀጥላል፡፡

በጉራጌ ባህል ለጀፎረ (ባህላዊ አውራ መንገድ) የተቀመጠን መሬት አጥሮ ወደ ግል ግቢ መከለል በምንም መልኩ የተወገዘ ነው፡፡

በጉራጌ የጀፎረ ፋይዳው የጎላ ነው። ለአብነትም ማህበራዊ ክንውን የሚከናወኑበት÷ ሰው ሲሞት የለቅስ ስርዓት የሚከናወኑበት÷ የሰርግ ስነ ስርዓት የሚከናወንበት የሙሽራውና የሙሽሪት አጀቦች በዘፈን ግጥም የሚሞጋገዙበት÷ ህጻናት የሚቦርቁበት ጎረምሶች የገና ጨዋታ የሚጫወቱበት÷ ዳመራ የሚቃጠልበት÷ ወጣቶች ፈረስ ጉግስ የሚለማመዱበት÷ ፈረስና በቅሎ የሚገራበት÷ ኮርማዎች እርስ በርሳቸው የሚፈታተሹበት÷ የሚያጓሩበት÷ ከብቶች የሚውሉበትና የሚጠበቁበት÷ ሽማግሌዎች ስለማህበራዊ ህይወታቸውና አጠቃላይ ኑሮአቸው በጋራ የሚመክሩበት÷ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት የሚከናወንበት÷ መንገደኛ ያለአንዳች ችግር የሚጓዝበት ነው፡፡

ፋይዳው እጅግ በጣም ብዙ የሆነው የጉራጌ ህዝብ ባህላዊ እሴት በአለም ቅርስነት ተመዝግቦ እውቅና እንዲያገኝ ሁላችንም ልንከባከበው ይገባል፡፡

https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid0362EvoBFYvZGJa2U8EkB88DmwjMYLQN4swwheyDHWYqyeQW5on8cf9y6vX6yJx2W4l/?app=fbl