Get Mystery Box with random crypto!

በዳውሮ ዞን ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም በጥላቻ ንግግርና በሀሰተኛ መረጃ የግል ተበዳዩን ስብዕና ያጎ | የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

በዳውሮ ዞን ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም በጥላቻ ንግግርና በሀሰተኛ መረጃ የግል ተበዳዩን ስብዕና ያጎደፈ ተከሳሽ በእስር ተቀጣ።

በዳውሮ ዞን የታርጫ ከተማ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሀምሌ 04/2014 የዋለው ችሎት የማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም በጥላቻ ንግግርና በሐሰተኛ መረጃ የግል ተበዳዩን ስብዕና ባጎደፈው ተከሳሽ በአቶ መርክነህ ማሞ ሚልካኖ ላይ የአንድ አመት ቀላል እስራት ውሳኔ አስተላልፏል።

ተከሳሹ የማህበራዊ ሚዲያ (Facebook) በመጠቀም በግል ተበዳይ ላይ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት የተበዳዩን ስም ከማጥፋትና ስብዕና ከማጉደፍም ባለፈ ግል ተበዳዩ በሚሰራበት አከባቢና መስርያ ቤት አመነታ እንዲያጣ እንዳደረገም የክስ መዝገቡ አብራርቷል።

በተከሳሹ ላይ የተላለፈው የእስር ውሳኔ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 እና አንቀፅ 7(ሀ) ስር የተደነገገውን አዋጅ ጥሶ በመገኘት መሆኑን የፍ/ቤት መረጃ አመላክቷል።

ይህ አይነት ወንጀል በአከባቢው የግለሰቦችን ስም በማጥፋት ግለሰቦች ተረጋግተው ስራ እንዳይሰሩ፣ ማህበረሰቡ በመንግስት ተቋማት አሰራር ላይ አመነታ እንዲያጡና እንዲሁም ግለሰቦች በሚኖሩበት አከባቢ ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸውን መልካም ግኑኝነትን በማጥፋት በአከባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዳይሰፍን የሚያደርግ እንደሆነ በቅጣት መዝገብ ላይ ሰፍሯል።

በመሆኑም በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት የተሰማራ አካል ካለ ከእንደዚህ አይነት አከባቢውንም ሆነ ግለሰቦችን ከማይጠቀም ተግባር እንዲቆጠቡ ጥሪ ያቀረበው ፍ/ቤቱ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ሚዲያን ለልማትና ለመልካም ነገር እንዲጠቀሙ ማሳሰባቸው የዳውሮ ዞን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን መምሪያ ዘግቦታል።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100068870753847
Telegram:-https://t.me/gummerw
Youtub:-https://youtube.com/channel/UCyqat__kk7lXxzpRv8r7chA