Get Mystery Box with random crypto!

በኦሬገን የአለም አትሌትክስ ሻምፒዮና ላይ አለም የሚያየው ሌላ አዲስ ፊት አለ~ አትሌት ኤርሚያስ | የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

በኦሬገን የአለም አትሌትክስ ሻምፒዮና ላይ አለም የሚያየው ሌላ አዲስ ፊት አለ~ አትሌት ኤርሚያስ ግርማ ከጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ

በ800 ሜትር ሀገሩን ይወክላል።

አትሌቱ ትውልዱ በጉራጌ ዞን ኧዣ ወረዳ የወንበር ቀበሌ ሲሆን በ2008 አዲስ አበባ ለትምህርት ወንድሙ ጋ ይመጣልና ከትምርቱ ጋ ስፖርት መስራትን ይጀምራል።

በኋላም ከወንድሙ ጋር በመሆን ኮልፌ ክፍለ ከተማ ሄዶ ወንዱሙ በቴኳንዶ ስፖርት እሱም በፍላጎቱ በአትሌትክስ ስፖርት ይመዘገብና ሩጫን ይጀምራል፤ በክፍለ ከተማውም በአሰልጣኝ ደምመላሽ ከበደ እየሰለጠነ ስልጠናውን ሊጨርስ የተወሰነ ጊዜ እንደቀረው የኢትዮጰያ ስፖርት አካዳሚ ማስታወቂያ ያወጣል÷ ክፍለ ከተማውም በአካዳሚው እንዲወዳደር ያስመወገበውና ይፈተናል፤

በተሰጠው የማጣሪያ ፈተናም አምስተኛ ደረጃ ቢወጣም በፈታኝ አሰልጣኞች እይታ በተለይ ደግሞ በመካከለኛ ርቀት አሰልጣኝ በሆነው በአቢዮት ተስፋዬ ግፊት በ2010 በአካዳሚው እንዲያዝ ተደረገ።

ሁሉ ነገር በተሟላበት የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚም በሚገባ እየሰለጠነ አትሌቱ ከጊዜ ወደጊዜ መሻሻሎችን እያሳያ ፈጣን ለውጦችን እያሳየ የመጣ አትሌት ነው።

በአካዳሚው በአሰልጣኝ አቢዮት ተስፋዬ እየሰለጠነ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ገና ከአካዳሚው ተመርቆ ሳይወጣ እነዚህን ፈጣን ሰዓቶች አስመዘገበ።
1:54, 1:49, 1:47 ,1:44.36

በአካዳሚው እያለ የልጁን አቅም ያዩ ክለቦች ገና ከመጀመሪያው ጀምሮ ቢያጭቱም ከአካዳሚው ተመርቆ ሳይወጣ ክለብ መያዝ ስለማይችል የክለቦች ፍላጎት ሳይሳካ ቢቀርም አትሌቱን ሲከታተል የቆየው የሲዳማ ቡና አትሌትክስ ክለብ ዘንድሮ በ2014 ሰኔ ላይ እንደተመረቀ የኔ ነህ ብሎ ወስዶታል።

አትሌቱ በአሰልጣኝ አቢዮት ተስፋዬ እየሰለጠ በግሎባል ስፖርት ማኔጅመንት ተይዞ የውድድር እድል ተዘጋጅቶለት ከላይ የተመዘገቡትን ፈጣን ሰዓቶች አስመዝግቦ ለኦሬገኑ የአለም አትሌትክስ ሻምፒዮና ላይ እና በኮሎቢያ ካሊ በሚደረገው የአለም ከ20 አመት በታች አትሌትክስ ሻምፒዮና ላይ ሀገሩን እንዲወክል ተመርጧል።

ልጁ እጅግ በጣም መልካም ስነስርዓት ያለው አትሌት ሲሆን አሯሯጡ ይመስጣል÷ እኔ ብዙ ኢትዮጵያጵያዊያን አትሌቶች ባደንቅም አሯሯጣቸው የሚስበኝ አሉ በተለይ የቀነኒሳ÷ የሲሳይ ለማ÷ የጥሩነሽ የሌሎችም የተወሰኑ አትሌቶች አሯሯጥ ያስደምመኛል÷ የዚህ ልጅ ግን ይለያል!!

ሩጫ የምትጠላ እንኳ ብትሆን ይህ ወጣት አትሌት ልጅ ሲሮጥ ካየህ በሩጫ ሰፖርት ፍቅር ትጠመዳለህ።

የልጁ አሯሯጥና ቁመና ሁሉ ነገር ስታይ ወይ የተፈጥሮ ማዳላት ትላለህ? ልጁንም ድንገት ብታገኘው እባክህ እስኪ ሩጥልኝ ትለዋለህ !!

ኳስ ሮናልዲኖህ ጎቹ እግር ላይ እንደምታምርና እንደምትሰቃይ ሁሉ ሩጫም እዚህ ልጅ ጋ ተጠቃልላ ገብታለች።

ብቻ ልጁ፣ ክለቡ፣ አሰልጣኙ እንዲሁም ማኔጅመንቱ በጋራ ተናበው ከሰሩ አትሌቱም በዚሁ ስነስርዓቱ ከቀጠለ የስፖርቱን ዲስፕሊን ካከበረ ኢትዮጵያ ሌላ ጀግና ታፈራለች።

ይህን ወጣት አትሌት በመጀመሪያ ያሰለጠነ እንዲሁም ለአካዳሚው የመለመለ ባለሙያ "የንስር አይን" ብዬ እይታውን እያደነኩ አካዳሚም ከገባ በኋላ አካዳሚውና ለልጁ እዚህ ደረጃ መድረስ አስተዋፅኦ ያደረጉ ከውስጥም ከውጭም ያሉ በሙሉ ሊመሰገኑ ይገባል እላለሁ።

መልካም የውድድር ዘመን!!

@ethio runners


https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid02ADEW8sA4JKE38VdcW8NmgD9ZJZ1GdLNvm9SbD1kRkGMSJxugw9n2h68yBpzP6s38l/?app=fbl