Get Mystery Box with random crypto!

ሀምሌ 06/2014 ዓ.ም በአበጃይ ትምህርት ቤት ከ10 ሺህ በላይ ችግኞች ተተከለ ጄዛንዳ የልማ | የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

ሀምሌ 06/2014 ዓ.ም

በአበጃይ ትምህርት ቤት ከ10 ሺህ በላይ ችግኞች ተተከለ

ጄዛንዳ የልማትና የአንድነት ማህበር 10 ሺህ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በአበጃይ ትምህርት ቤት ተክሏል።

ማህበሩ 3ተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራና የልማት ፕሮግራሙ የወረዳው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች÷ የማህበሩ ዋናና ምክትል ሰብሳቢዎች እንዲሁም የማህበሩ የከተማና የገጠር አባላት በተገኙበት በአበጃይ ሁለተኛ ትምህርት ቤት አካሂዷል።

የጄዛንዳ የልማትና የአንድነት ማህበር ሰብሰቢ አቶ መሀመድ ውድማ እንደገለፁት ማህበሩ ከዚህ በፊት ትምህርት ቤቱ ላይ ተምረው ባለፉ ተማሪዎች የተቋቋመ መሆኑን ገልጸዋል።

ማህበሩ የልማት ስራው መስራቾቹ ባሉበት በአበጃይና በአካባቢዋ የጀመረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊና ድንበሯ ለማዳረስ አላማ አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

አቶ መሀመድ አክለውም ማህበሩ ዛሬ ባካሄደው 3ተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 10 ሺህ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የምግብ፣ የውበትና የገቢ ምንጭ የሚሆኑ ችግኞች መሆናቸውን አብራርተዋል።

ማህበሩ ለአይደራ፣ ለአሰለጫ፣ ለእንጀፎ፣ ለአበጃይ አንደኛና ሁለተኛ፣ ለሰነን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንና ለጉርአምባ መስጂድ የውበት ችግኞች በስጦታ አበርክቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በወረዳው በአረቅጥ ከተማ በሆቴሉ ዘርፍ ተሰማርቶ ለህብተረሰቡ አገልግሎት እየሰጠ ለሚገኘው ግጥም ካፌም የውበት ችግኞችና ልበ ወለድ መፅሐፍቶች በስጦታ ማበርከታቸውን ሰብሳቢው ተናግረዋል።

ከልማትና ከአረንጓዴ አሻራ ስራው ጎን ለጎን 220 ሺህ ብር ወጪ በማድረግ በወረዳው ከአይደራ፣ ከአሰለጫ፣ ከእንጀፎ፣ ከአበጃይ አንደኛና ሁለተኛ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡና ከየትምህርት ቤታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የቦርሳና የማጣቀሻ መፅሐፍት ድጋፍ በማድረግ ተማሪዎቹን አበረታቷል።

በፕሮግራሙ የተገኙት የጉመር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደገሙ አለሙ በበኩላቸው÷ ማህበሩ ለትውልድ የሚተላለፍ ልማቶች ለይቶ ወደ ስራ መግባቱ የሚበረታታና በቀጣይም ለበለጠ ስራ የሚያደርስ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይ የወረዳው መንግስት የማህበሩ ጋር በመሆን በማህበሩ የተጀመሩ በጎ ጅማሮዎች ለማስቀጠል በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል ሲል የዘገበው የጉመር ወረዳ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!


https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid0dqEnqVYRfbnLKmQHd6WUhe2b68WSm479nrSsExdXs1gPFXdXPymTc2aVt6W6AEEUl/?app=fbl