Get Mystery Box with random crypto!

ላይ ሳሉ ነበር!……ጥቁር እንግዳ የመጣባቸው ሴት ተማሪዎች በሙሉ ከመቀመጫቸው ሲነሱ አንዲት ሴት ብ | ከመፃህፍት ገፆች

ላይ
ሳሉ ነበር!……ጥቁር እንግዳ የመጣባቸው ሴት ተማሪዎች በሙሉ
ከመቀመጫቸው ሲነሱ አንዲት ሴት ብቻ ምንም እንዳልተፈጠረ በመቁጠር
ገበታዋ ላይ አቀርቅራ ቀረች። በክብራቸው የማይደራደሩት ጃንሆይ፦"ምነው
ቆንጂት አንቺ አትነሺም!?" አልዋት። እሱዋም ወደገበታው እያሳየች በድፍረት፦"
እዚህም ሌላ ንጉስ አለ……እሱን ጥዬ እንዴት?" አለቻቸው።
ብልዕነት ያዘለ መልስዋ፤ በራስ መተማመንዋና አንፀባራቂ ውበትዋ ታክሎበት
ጃንሆይ፦"ይቺማ የመኩዬ የወደፊት ውሃ አጣጪ ሚስት ናት!" ብለው ደመደሙ።
ምንም እንኩዋን ኃላ ላይ ከዚህች ሴት ጋር በደም ቢዛመዱም፤ ደምም
ተቃብተዋል ማለት ይቻላል!………የስርዓቱ ቀንደኛ ተቃዋሚና የተማሪዎች
የፖለቲካ ንቅናቄ መሪ የነበረው ጥላሁን-ግዛው ተመክሮና-ተዘክሮ እምቢ
በማለቱ አንድ ምሽት የፀጥታ ሰራተኞች እንደሆኑ በሚገመቱ ሰዎች በጥይት
ሕይወቱ አለፈ………ጃንሆይ የልጃቸው ሚስት ያደረጉዋት ያቺ ቆንጅዬ ተማሪ
ታዲያ የጥላሁን እህት፦"ሳራ-ግዛው" ነበረች።
ልዕልት ሳራ-ግዛው ዛሬም በህይወት ያለች ሲሆን፤ ከአመታት በፊት ዋቢ ሸበሌ
ሆቴል አንድ ፕሮግራም ላይ አይቼያት ፀጉርዋ በደማቅ ሽበት ሙሉ በሙሉ
ከመወረሩ በቀር ያ-የቀድሞ ውበትዋ ይዞታው ላይ ቁጭ ብሎ ይታያል።
ባለቤትዋ ልዑል መኮንን ግን ዛሬም እንዴት እንደሞተ እንቆቅልሽ ሆኖ የዘለቀ
ሲሆን፤ በሹክሹክታ በሰው እጅ ተገደለ ተብሎ ቢናፈስም……በወቅቱ ግን
በመንግስት የተሰጠው ኦፊሻላዊ የሞቱ መግለጫ የመኪና አደጋ የሚል ነበር።
የሞተውም ሞጆ መገንጠያ አካባቢ ሲሆን ቦታው ላይ ዛሬም ድረስ ለመታሰቢያ
ተብሎ ቤተክርስቲያን ተሰርቶበታል።
ጃንሆይ ያ-እንደአንበሳ ኮስታራ ገጻቸው ስሜቱን መቆጣጠር ሳይችል ቀርቶ
እንደተራ ሰው በአደባባይ ተንሰቅስቀው ሲያለቅሱ የታዩት ልዑል መኮንን የሞተ
ዕለት ነበር።ምን እሳቸው ብቻ? ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ ለልዑል መኮንን
ከማንባትም አልፎ ለአንድ ወር ጥቁር የሀዘን ልብስ ለብሶለታል። ይሄ ታዲያ
የንጉስ ልጅ ስለሆነ ለማሽቃበጥ ሳይሆን ከልብ በመነጨ የተደረገ የሃዘን ምላሽ
ነበር። የደግ ሰው ማረፊያ ከልብ ወዲያ የት ይሆናል? ልዑል መኮንን እጅግ
ሲበዛ የዋሕ እና ድሆችን መርዳት የሚወድ ለጋስ ሰው ነበር።
የሰው ችግር በቀላሉ የሚገባው፤ በቅንጦት ፓላስ ውስጥ ቢያድግም ታች
የሳጠራ ቤትና ጎዳና ላይ ሌሎች ነብሳት እንደሚኖሩ በተፈጥሮው የገባው የድሃ
አባት ነው። የራበው ካየ ችሎና ጨክኖ አያልፍም፤ አንድ ጊዜ አራዳ ጊዮርጊስ
ቤተክርስቲያን ተሳልሞ ሲወጣ በራፉ ላይ ትኩስ አራስ የታቀፈች እመጫት
ተመለከተ። ኪሱ ቢገባ ምንም የገንዘብ ዘር አጣ……ምን ያድርግ? ቀጥታ የሞሃ-
አንበሳ ዓርማ ያለበትን የወርቅ ቀለበት ከጣቱ ላይ አወለቀና ለእመጫይቱ፦'
እንኪ ሽጪና ተጠቀሚ!" ብሎ ሰጣት።
ሴትዮዋ ለአንጥረኞች ወስዳ ስታሳያቸው ባዩት ነገር ደነገጡ፦የቤተመንግስት
ቅርስ መሆኑን እንዳወቁ ይሄን በወርቅ በግብይት ከመዳፈር ይልቅ ጉዳዩን
ለቤተመንግስቱ አስተዳደር አቤት አሉ። ጉዳዩ እንደቀልድ ጃንሆይ ጆሮ ደረሰና
ሴትዮዋና አንጥረኞቹ ጃንሆይ ዘንድ ቀረቡ……ወርቁ ከማን እንደተሰጣት ጥቂት
ሰምተው ወዲያው ገባቸው!!…የልጃቸው የልዑል መኮንን ደግነት እንደውቅያኖስ
የሰፋ መሆኑን ያውቁታል።
ስለዚህ በቀጥታ ወደአንጥረኞቹ ዞረው፦" ይሄን ወርቅ አሁን ባለው ገበያ
ብትገዝዋት ምን ያህል ተመን ትከፍሉዋት ነበር!?" አሉዋቸው። አንጥረኞቹ
በግራም አስልተው ዋጋውን ሲናገሩ ጃንሆይ ሂሳቡን አምስት ሳንቲም ሳያስቀሩ
ለሴትዮዋ ቆጥረው ሰጥዋት።