Get Mystery Box with random crypto!

በምስሉ የሚታዩት የጃንሆይ ልጆች ሴቷ ተናኜ ወርቅ ስትሆን፣ ትልቁ ወንድ ልጅ አልጋ-ወራሽ ልዑል አ | ከመፃህፍት ገፆች

በምስሉ የሚታዩት የጃንሆይ ልጆች ሴቷ ተናኜ ወርቅ ስትሆን፣ ትልቁ ወንድ ልጅ
አልጋ-ወራሽ ልዑል አስፋው-ወሰን ሲሆን ትንሹ ልዑል መኮንን ነው። ወንዶቹ
ሁለቱ በባሕሪይ ፍፁም የተለያዩ ሲሆን አስፋወሰን የወደፊቱ ንጉስ ነውና
ጠንቃቃ፤ ወግ-አጥባቂ፤ ራሱን ለወደፊቱ ስልጣን ሲል የሚጠብቅ ሲሆን ልዑል
መኮንን ግን በፍፁም የቤተመንግስት ስርዓት እግሮቹን ያላሰሩት ነፃና ጭሰት
የሚወድ፤ የንጉስ ልጅ ነኝ በሚል ትዕምክት ያልተጠመደና ተራ ሆኖ ከማንኛውም
ዜጋ ጋር ተደባልቆ የሚኖር ስብዕና ነበረው። መዝናናትና ሳቅ ቀለቦቹ ሲሆኑ እነ-
አባባ ተስፋዬን ይዞ በየክለቡ የሚዞር እንዲሁም ኃይለኛ ሴት ጠባሽ እንደነበርም
ይነገርለታል።
ውድ መኪና ይዞ ከቤተመንግስት ያለቦዲጋርድ ከወጣ በኃላ ማንኛውም ተራ
ሰው ከሚዝናናበት ቦታ የእረፍት ጊዜውን ያሳልፋል። ጃንሆይ በአባታቸው ስም
የጠሩት ይሄ ልጃቸው የዓይናቸው ብሌን ያህል የሚሳ ሱለት ሲሆን፤ እንዴት
እንደሚወዱት ለታዘበ ሌላ ልጅ የሌላቸው ይመስላል። ሚስት ያጩለት እንኩዋን
ራሳቸው እንደሆኑ ይነገራል፣ የልዑል መኮንን ሚስት ተደርጋ የታጨችው ሴት
በአንድ ወቅት ተማሪ ሳለች ት/ቤታቸውን ለመጎብኘት ጃንሆይ ይመጣሉ።
የመጡበት ሰአት ደግሞ ተማሪዎቹ በመመገቢያ አዳራሽ ምግብ በመብላት