Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም እንዴት አደራችሁ ፍቁራንና ፍቁራት? መልመጃ መልስ የአረብኛ ቊጥሮችን ወደ ግእዝ አኀዝ | ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)

ሰላም እንዴት አደራችሁ ፍቁራንና ፍቁራት?

መልመጃ መልስ

የአረብኛ ቊጥሮችን ወደ ግእዝ አኀዝ መቀየር

ሀ) 189

1 89
፩ | ፹፱


= ፩፻፹፱ = ፻፹፱ (አሐዱ ምእት ሰማንያ ወተሠዓቱ)

ለ) 325

3 25
፫ | ፳፭

= ፫፻፳፭ -- ሠልስቱ ምእት እሥራ ወኃምስቱ

ሐ) 402

4 02
፬ | ፪

= ፬፻፪ -- አርባዕቱ ምእት ወክልኤቱ

መ) 4002
40 02
፵ | ፪

= ፵፻፪ -- አርብዓ ምእት ወክልኤቱ

ሠ) 6875
68 75
፷፰ | ፸፭


=፷፰፻፸፭ -- ስድሳ ወስመንቱ ምእት ሰብዓ ወኃምስቱ

ረ) 8000

80 00
፹ | --

=፹፻ ሰማንያ ምእት