Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለክሙ አኃውየ ወአኃትየ። እስኪ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ተወያዩባቸው ምልማድ ፩ ትክክ | ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ)

ሰላም ለክሙ አኃውየ ወአኃትየ።

እስኪ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ተወያዩባቸው

ምልማድ ፩

ትክክለኛ መልስ የያዘ ነው ብላችሁ
የምታስቡትን ፊደል ምረጡ።

፩. መሠረታዊ (መደበኛ) የግእዝ ፊደላት (አዕጹቃቸውን ሳይጨምር) ብዛት ስንት ነው?
አ) 182 (፻፹፪)
በ) 26 (፳፮)
ገ) 202 (፪፻፪)

፪. ከሚከተሉት ውስጥ የግእዝ ፊደላትን ብቻ ያልያዘው ስብስብ የቱ ነው

አ) ሀ፣ለ፣ሐ፣መ፣ሠ፣ረ
በ) ሸ፣ቨ፣ቸ፣ኘ፣ኸ፣ዠ፣ጀ፣ጨ
ገ) ቀ፣ ወ፣ ገ፣ ቐ፣ኧ፣ ቛ፣
ደ) ደ፣ ሐ፣ ዘ፣ ከ፣ ጸ፣ ዐ


፫. "አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን ይቅር በለን" ለማለት የቱን እንጠቀማለን?

አ) እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
በ) እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ

፬. "አበበ የቤት ሥራውን ጨረሰ" ለማለት ትክክለኛው የቱ ነው

አ) አበበ የቤት ሥራውን ፈጸመ
በ) አበበ የቤት ሥራውን ፈፀመ

፭. ከሚከተሉት ውስጥ በትክክል የተጻፈው የቱ ነው?

አ) ቃለ ህይወት ያሰማልን
በ) ቃለ ሕይወት ያሰማልን
ገ) ቃለ ኅይወት ያሰማልን

፮. "ክርስቶስ ከድንግል ተወለደ" የሚለው አቻ ትርጒሙ የቱ ነው?

አ) ክርስቶሰ ሰረቀ እምድንግል
በ) ክርስቶስ ሠረቀ እምድንግል
(እምድንግል = ከድንግል)

፯. የሰው ልጆች ሁሉ አባት፣ በእግዚአብሔር እጅ የተፈጠረው ሰው ስም የቱ ነው?

አ) ዐዳም
በ) አዳም


፰.የፀሓይ መግቢያን የሚያመለክተው፦
አ) ምእራብ
በ) ምዕራብ

፱. በትክክል የተጻፈው ስመ ክርስትና የቱ ነው?

አ) ወለተ ስላሴ
በ) ወልደ መድህን
ገ) አመተ ሥላሴ
ደ) ዓመተ ሥላሴ

፲. የፀሓይ መውጫን የሚያመለክተው፦
አ) ምስራቅ
በ) ምሥራቅ


፲፩. ከታች የተሰጠን የሁለት ተጋቢዎች በጋብቻቸው ዕለት የተጻፈላቸው ጽሑፍ ነው እንበል። በትክክል የተጻፈው የቱ ነው?

አ) የአቶ ዐምደወርቅ እና ወይዘሮ ሰብለወንጌል ሰርግ መርሐ ግብር

በ) የአቶ ዐምደወርቅ እና ወይዘሮ ሰብለወንጌል ሠርግ መርሐ ግብር


፲፪. በትክክል የተጻፈው የቱ ነው?
አ) መድሀኔአለም
በ) መድኃኔዓለም
ገ) መድሐኔዓለም
ደ) መድሐኔአለም

፲፫. ሥዕል መሳልን የሚያመለክተው

አ) ሰአለ
በ) ሠዓለ


፲፬. እመቤታችን በየወሩ በ፲፮(16) ትከብራለች። የስሟ መጠሪያ በትክክል የተጻፈው የቱ ነው?

አ)ኪዳነ ምኅረት
በ)ኪዳነ ምህረት
ገ)ኪዳነ ምሕረት
ደ)ኪዳነ ምኽረት


፲፭. በትክክል የተጻፈው የቱ ነው?
አ) ሃይማኖት
በ) ሐይማኖት
ገ) ኀይማኖት
ደ) ሓይማኖት


፲፮. ሰው ስለ ኀጢአቱ ተጸጽቶ ወደ
እግዚአብሔር የሚመለስበት ምን ይባላል፦

አ) ንሥሀ
በ) ንስኀ
ገ) ንስሐ
ደ) ንሥኸ


፲፯. አባቶች የሚሰጡት ተግሳጽና ቡራኬ ምን ይባላል?
አ) ምዕዳን
በ) ምእዳን

አጭር መልስ ስጡ

፲፰. የ "የ"ን አዕጹቅ/ቅጥያ ከግእዝ እስከ ሳብዕ ጻፉ

፲፱. ግእዝ ማለት ምን ማለት ነው?

፳. የውስጣችሁን ስሜትና ምኞት መልሱ

ሀ) ግእዝ ቋንቋ ለመማርም ምን አነሳሳችሁ?
ለ)እናንተ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ማዕከል ኃላፊ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?
ሐ) ወደፊት ቤተሰብ ስትመሠርቱ (የመሠረታችሁ ካላችሁም) በግእዝ ልሳን ጉዳይ ምን ለማድረግ ትመኛላችሁ