#IFTAR
ዛሬ በደሴ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ይካሄዳል።
ለዚህም ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ።
ከደሴ ከተማ ኮሚኬሽን ቢሮ ባገኘነው መረጃ ዛሬ ሀሙስ የሚካሄደው ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት እንደ አምናው " ኑ በጋራ እናፍጥር" በሚል ሲሆን ለደሴ ከተማ የክርስትና እምነት የተከታዮችም " ኑ በጋራ እናፍጥር " ውብ የሆነውን የወሎን እሴት እናስቀጥል የሚል ጥሪ ቀርቧል።
በሌላ መረጃ ነገ ቅዳሜ ረመዳን 15 (ሚያዚያ 8) በድሬዳዋ ከተማ " የአብሮነት ኢፍጣር በድሬዳዋ " በሚል በምድር ባቡር ለገሃር አደባባይ ይካሄዳል፤ በዕለቱ በአብሮነት ከማፍጠር ባለፈ የቁርዓን እጥረት ላለባቸው ከተሞች ቁርዓን የሚሰበሰብ ሲሆን እስከ 1000 ቁርዓን ለማሰባሰብ ታቅዷል።
በተጨማሪ የፊታችን እሁድ ሚያዚያ 9 በኮምቦልቻ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት መዘጋጀቱ ተሰምቷል።
እንዲሁም በሀረር ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሚያዚያ 9 ከራስ ሆቴል እስከ ጁምዓ መስጂድ ድረስ ይካሄዳል ተብሏል።
በሌሎችም የሀገራችን ከተሞች ላይ ተመሳሳይ ስነ ሥዓቶችን ተከታትለን እናሳውቃለን።
ፎቶ ፦ ደሴ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT