Get Mystery Box with random crypto!

#MoE የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎችን አፈፃ | Free Education Ethiopia ✔️︎

#MoE

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎችን አፈፃፀምን በተመለከተ ለህ/ተ/ም/ቤት ባቀረቡት ሪፖርት የ2015 የፈተና ዝግጅትን በተመለከተ አብራርተዋል።

ለ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ፣ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በየትምህርት አይነቱ እራሱን የቻለ የፈተና ዝግጅት ቢጋር እንዲዘጋጅ ተደርጓል ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፤ " የ12ኛ ክፍል ዋናና የሙከራ ፈተና በፈተና በቢጋሩ መሰረት ከተለኪ ባህሪያት አንፃር ተገቢና አስተማማኝ ጥያቄዎችን በጥንቃቄና #ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ በተዘጋጀ የስራ መመሪያ ቼክ ሊስት መሰረት በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከቀናት በፊት ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ #በመንግስት_ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe