Get Mystery Box with random crypto!

አገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡባቸው እና የምረቃ ቀናት እንዲሁም የሬሜዲያ ፈተና ወጤት አያያዝ ላይ | Free Education Ethiopia ✔️︎

አገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡባቸው እና የምረቃ ቀናት እንዲሁም የሬሜዲያ ፈተና ወጤት አያያዝ ላይ ቅያሪ ተደርጓል።

- በ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ ፤ ተቋማት ፊተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 30 ከመቶ፣ #በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 70 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

- በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ ውጤት ሐምሌ 10 ቀን የሚገልጽ ይሆናል ተብሏል።

- የተማሪዎችን ምረቃ በተመለከተ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው ብሏል።

- የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!