Get Mystery Box with random crypto!

ዘንድሮ 240 ሺህ ሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል። በ201 | Free Education Ethiopia ✔️︎

ዘንድሮ 240 ሺህ ሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል።

በ2015 በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰበሰበው መረጀ መሠረት 240 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በበይነ-መረብ የመውጫ ፈተና ለመስጠት መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ይህ ያስታወቀው የ9 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለህ/ተ/ም/ቤት እያቀረበ በመገኝበት በአሁን ሰዓት ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ በ2015 በመጀመሪያ ዲግሪ ኘሮግራም ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ብሉ -ኘሪንት የተዘጋጀ መሆኑና የመውጫ ፈተና የክፍያ ተመን ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱን ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት አብራርተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናን ለመተግበር የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱንም የገለፁት ሚኒስትሩ፤ የመውጫ ፈተና ስትራቴጂ ማስፈፀሚያ መመሪያ እና የድርጊት መርሃ-ግብር ዝግጅት መጠናቀቁንም አብራርተዋል፡፡

በመውጫ ፈተና የሚካተቱ የትምህርት ዓይነቶች (ኮርሶች) ተለይተው፤ በቅድመ-ምረቃ በሚሰጡ በሁሉም የትምህርት መስኮት የፈተና ንድፍ ማሳያ መዘጋጀቱንም አስረድተዋል፡፡

መረጃው የህ/ተ/ም/ቤት ነው።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe