Get Mystery Box with random crypto!

'' መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የውትድርና ስልጠና ወስደው ብሔራዊ አገልግ | Free Education Ethiopia ✔️︎

'' መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የውትድርና ስልጠና ወስደው ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ይችላል " - ዲማ ኖጎ ( ዶ/ር)

መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች  በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ሊያደርግ እንደሚችል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።

ሰብሳቢው ይህንን ያሳወቁት ዛሬ የሕዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት የመከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል  የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ  ባጸደቀበት ወቅት ነው፡፡

ዶ/ር ዲማ  ናጎ ምን አሉ ?

" ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዕድሜያቸው 15 ዓመት የሞላቸው እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ሊያደርግ ይችላል።

ተማሪዎች በፈቃዳቸው በመደበኛ የመከላከያ ሠራዊት ወይም የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል አባላት የሚሆኑ ከሆነ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተያያዥ መብቶችንና ጥቅሞች እንዲጠበቁላቸው ያደርጋል። "

የተሻሻለው የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ ሆኖ የተጣለበትን ሀገር የመጠበቅ ተልዕኮ በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲወጣ የሚያስችል ነው ተብሏል።

የተሻለ ሠራዊት ለመገንባት ማነቆ የሆኑ ሕግ ማዕቀፎችን እና ተቋማዊ አስተሳሰቦችን በመፈተሽ ለሀገር እና ሕዝብ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ነው የተገለፀው።

ምክር ቤቱ በተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1286/2015 አድርጎ   በስድስት ድምጸ-ተኣቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

Via HoPR
@Free_Education_Ethiopia