Get Mystery Box with random crypto!

#ብሔራዊ_ፈተና ' እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም ' - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግ | Free Education Ethiopia ✔️︎

#ብሔራዊ_ፈተና

" እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች የፈተና ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ/ም ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ ፥ ማንኛውም የስም፣ የፆታ፣ የተፈጥሮ/የማህበራዊ ዘርፍ እና የፎቶ ማስተካከያ ከፈተና በፊት ስለማይደረግ እያንዳንዱ ተፈታኝና እና መዝጋቢ ትክክለኛነቱን የማጣራትና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት ብሏል።

ይህ መሆን ያለበትም ምዝገባው በበየነ መረብ በመሆኑ በትምህርት ቤት ደረጃ የተካሄደው የምዝገባ መረጃ በቀጥታ በማንም ሳይነካ ወደ ተቋሙ የመረጃ ቋት የሚገባ በመሆኑ ነው ሲል አስረድቷል።

ከሚያዚያ 20/2015 ዓ/ም በኋላ በግለሰብ ወይም በተቋም በኩል የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን #አላስተናግድም ሲል በጥብቅ ያሳሰበው አገልግሎቱ ፥ ፈተናው የሚሰጠው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥና የመፈተኛ ጊዜን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚገለፅ አሳውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፥ እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም ያለ ሲሆን ተፈታኞች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!