Get Mystery Box with random crypto!

ፍኖተ ኦርቶዶክስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ finoteorthodox — ፍኖተ ኦርቶዶክስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ finoteorthodox — ፍኖተ ኦርቶዶክስ
የሰርጥ አድራሻ: @finoteorthodox
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.41K
የሰርጥ መግለጫ

የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ሥርዓት እና አስተምህሮ የጠበቀ #ትምህርተ_ሃይማኖት ይሰጣል፡፡ በተለይ #ጥያቄዎቻችሁ መልስ ያገኛሉ ።
መንፈሳዊ ትምህርት በመማር የሕይወትን ማዕድ ይቋደሱ ለመቀላቀል 👇👇ይጫኑ
@finoteorthodox
@finoteorthodox

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-02-28 11:22:52 መልካም ዕለተ ሰንበት!!!
2.6K viewsፈለገ ጢሮስ, 08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-17 07:04:55
“በማንም ላይ ክፋትን አትሥሩ - አትፍረዱ! ይኽንን ከጠበቃችኹ ርስቱን ትወርሳላችኹና!

ታላቁ አባ መቃርስ
3.2K viewsዓውደ ቀመር, 04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-15 11:05:29
+++ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ አምላክ አሐዱ ውእቱ+++

ኵሉ ይሰግድ ለሥላሴ ፤ ወይትቀነይ ኵሉ ለመንግሥተ ሥላሴ፤
እስመ ኮነ ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል፤
ወበዓይኑ ይኔጽር ቀላያተ፡፡

እንኳን ሥሉስ ቅዱስ የባቢሎንን ግንብ ላፈረሱበት ዕለት እና ለቅዳሴ ቤታቸው ለከበረበት ዕለት በሰላም አደረሳችኹ!

ቅድስት ሥላሴ የእኛንም መለያየት እና የከበበንን መከራ እንደባቢሎን ግንብ አፍርሰው ለሕይወት ያብቁን!!
አሜን በእውነት!!!
3.0K viewsዓውደ ቀመር, 08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-11 16:36:50 ምክር!

ሰዎችድንጋይ ወደ አንተ ከወረወሩብህ ምክንያቱ ብዙ ፍሬ ያፈራ መልካም ዛፍ ሆነሃል ማለት ነው። በአንተ ውስጥ ለመብል የደረሱ ፍሬዎችን አይተዋል። ድንጋይ ሲወረውሩብህ በእነርሱ ልክ ወርደህ ድንጋይ አትመልስላቸው ይልቅ ድንጋይ ለሚወረውሩብህ ፍሬህን ስጣቸው ። በምትሰጣቸው ፍሬ ውስጥ ያለው ዘርህ ምን አልባት እነርሱን አነቃቅቶ መንገድ ያስቀይራቸዋል!
2.7K viewsዓውደ ቀመር, 13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-10 17:02:31 "ኦ ለዝንቱ መንክር ልዑል ላዕለ ኩሉ ሕሊናት ብእሲት ምድራዊት ወለደቶ ለእግዚአብሔር ቃል ዘኮነ ሰብአ፡፡ ድንግል ወለደቶ ለገባሪሃ ወለሊሁ ፈጠረ ወላዲቶ ወእምኔሃ ነስአ ሥጋነ ዘውእቱ ፈጣሪ"
"ከሕሊናት ሁሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ምስጢር አንክሮ ይገባል ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃልን ወለደችው ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ ከርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ"
(ሃይማኖተአበው ዘቅዱስ ኤፍሬም)
እንኳንለአምላካችን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
2.4K viewsዓውደ ቀመር, 14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-08 07:43:18

እንኳን ለአባ ዮሐንስ አበ ምኔት፣ ለአባ ዘካርያስ ገዳማዊ፣ ለአባ ዮሐንስ ብጹዕ እንዲኹም ለ"144 ሺ" ሕፃናት (ሔሮድስ የገደላቸው) ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ



ዳግመኛም ዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ፣ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት፣ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት፣ ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት እንዲኹም አባ ሣሉሲ ክቡር ጻድቅ ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን አሜን!

"የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯



@bisrategebrel @bisrategebrel
@bisrategebrel @bisrategebrel
2.3K viewsዓውደ ቀመር, 04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-07 17:39:49 እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!!!
2.0K viewsዓውደ ቀመር, 14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-06 12:36:44 #ሰብአ_ሰገል_ወርቅ_ዕጣንና_ከርቤ_የመገበራቸው_ምስጢር፡-

የጌታችንን ልደት በኮከብ ተረድተው ሰብአ ሰገል (የጥበብሰዎች)ማንቱሲማር፣ ሜልኩ በዲዳስፋ የተባሉ የፋርስ ነገሥታት ወርቅ፣ ዕጣን ከርቤ አምጥተው የመገበራቸው (አምሐአድርገው የመስጠታቸው)ምስጢር እንደምንድን ነው ቢሉ፡-

#ወርቅ፡-
ወርቅ መገበራቸው ይኸን የምንገብርላቸው ነገሥታት ቀድሞም ፍጡራን ኋላም ኀላፍያን ናቸው። አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርህ ነህ፤ ኋላም የማታልፍ ነህ ሲሉ፤ አንድም ወርቅ ጽሩይ ነው፤ ጽሩየ ባሕርይ ነህ ሲሉ፤ እንዲሁም በአንተ ያመኑ ምዕመናንም ጽሩያነ ምግባር ወሃይማኖት ናቸው ሲሉ። አንድም ወርቅ የሃይማኖት ምሳሌ ነው። የሃይማኖት ጽሩይነቱና ግብዝነቱ የሚታወቅ መከራ ሲቀበሉበት ነውና።

#ዕጣን፡-
ዕጣን መገበራቸው ይህንን የምናጥናቸው ጣዖታት ቀድሞም ፍጡራን ኋላም ኀላፍያን ናቸው። አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርህ ኋላም የማታልፍ ነህ ሲሉ። አንድም ዕጣን ምዑዝ ነው፤ አንተም በባሕርይ ምዑዝ ነህ ሲሉ እንዲሁ ደግሞ በአንተም የሚያምኑ ምእመናንን ምዑዛነ ምግባር ወሃይማኖት ናቸው ሲሉ። አንድም ዕጣን የተስፋ ምሳሌ ነው። ዕጣን ከሩቅ እንዲሸት ተስፋ ያልያዙትን እንደያዙት ያላዩትን እንዳዩት ታደርጋለችና።

#ከርቤ፡-
ከርቤ መገበራቸው ምንም ቀድሞ ያልተፈጠርህ በኋላም የማታልፍ ብትሆንም በሰውነትህ መራራ ሞትን ትቀበላለህ ሲሉ፤ አንድም ከርቤ የተሰበረውን ይጠግናል፤ የተለየውን አንድ ያደርጋል። አንተም ከማኅበረ መላእክት የተለየ አዳምን አንድ ታደርገዋለህ፤ ጽንዓ ነፍስ ሰጥተህ ታጸናዋለህ ሲሉ። አንድም በዕለተ ዓርብ ያቀምሱታልና ከርቤ አመጡለት። ከርቤ የምዕመናን ምሳሌ ነው። በፍቅር አንድ ይሆናሉና። ከርቤ የፍቅር ምሳሌ ነው። ከርቤ አንድ እንዲያደርግ ፤ ፍቅርም አንድ ታደርጋለችና።

በአጠቃላይ ሰብአ ሰገል ወርቅ፣ እጣን ከርቤ የገበሩለት ሃይማኖት፣ ፍቅር፣ ተስፋ፣ ገንዘቦችህ ናቸው ሲሉ ነው። በሌላ መልኩ ወርቅ ለመንግሥቱ፣ ዕጣን ለመለኮቱ፣ ከርቤ ለሞቱ ምሳሌ ናቸው።

@Bisrategebrel @Bisrategebrel
@Bisrategebrel @Bisrategebrel
2.4K viewsዓውደ ቀመር, 09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-03 11:24:15 ልብህ ሞልቷል

አንድ ወጣት ወደ አንድ መነኩሴ ዘንድ ይሄድና ክርስትናን ማወቅ እፈልጋለው ስለ ክርስትና ንገሩኝ አላቸው ። ና ልጄ ውስጥ ሻይ እየጠጣን እናውራ ብለው ወደ ባዕታቸው ይዘውት ገቡ ።ከዛ ማንቆርቆሪያቸውን ጥደው ሻዩ እስኪፈላ መጠበቅ ጀመሩ ። ልጁም በሚገርም የወሬ ፍጥነት አባ ክርስትና እንዲ ነው አይደል ፡አባ ክርስትና እንደዛ ነው አይደል ?ሰዎች እኮ ነግረውኛል እያለ ከሰዎች የሰማውን ይቀባጥራል

መነኩሴውም ዝም ብለው ሲሰሙት ቆዩና ሻዩ ሲፈላ ብርጭቆ አምጥተው ይቀዱለት ጀመረ ። ብርጭቆው ሞልቶ እየፈሰሰም ዝም ብለው ይቀዳሉ ። ከዛ ልጁም አንተ መነኩሴ ያምሀል እንዴ ?ብርጭቆውኮ ሞልቷል ። አንተ ለምትጨምርበት ሻይ ቦታ የለውም አላቸው ። መነኩሴውም አየህ ልጄ አንተም እንደዚ ብርጭቆ ነህ ። ስለ ክርስትና ማወቅ ትፈልጋለህ ነገር ግን ልብህ ሌሎች በነገሩህ አሉባልታ ተሞልቷል እኔ የምነግርህን ነገር የምትቀበልበት ቦታ በልብህ ውስጥ የለም

ብነግርህም ታፈሰዋለህ ። ስለዚህ አሁን ሂድ ልብህ ባዶ ሲሆን ተመልሰህ ና ያኔ እነግርሃለው አሉት። እኛስ ዛሬ ልባችንን የሞላው ምንድነው ?ፍቅር ?ሰላም ?መቻቻል ?ታምኝነት ፣ ህብረት አንድነት ነው ወይስ አስቀድሞ ልባችን በተንኮል ፣ በሟርት ፣ በቅናት፣በሴሰኝነት ፣ በዘረኝነትና በጎጠኝነት ስለተሞላ ለመልካም ነገሮች ቦታ የለውም ?እስቲ እራሳችንን እንፈትሽ ልባችንን ሞልቶት እየፈሰሰ ያለው ምንድነው ?

@bisrategebrel
@bisrategebrel
2.7K viewsTRIDENT, 08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-30 09:48:09
‟መብረቅ ሲጮህ ሰው ሁሉ እንደሚደነግጥ የአንቺንም ስም ሲሰማ ዲያቢሎስ ይደነግጣል። አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ እረፍት አላገኘምና ነው። በአንቺ ታመመ በልችሽ መስቀል ተሰቃየ ስለሆንም ከፍጥረት ሁሉ አንቺን ይጠላል”።
(ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

እንኳን አደረሳችሁ
2.4K viewsTRIDENT, 06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ