Get Mystery Box with random crypto!

ልብህ ሞልቷል አንድ ወጣት ወደ አንድ መነኩሴ ዘንድ ይሄድና ክርስትናን ማወቅ እፈልጋለው ስለ ክ | ፍኖተ ኦርቶዶክስ

ልብህ ሞልቷል

አንድ ወጣት ወደ አንድ መነኩሴ ዘንድ ይሄድና ክርስትናን ማወቅ እፈልጋለው ስለ ክርስትና ንገሩኝ አላቸው ። ና ልጄ ውስጥ ሻይ እየጠጣን እናውራ ብለው ወደ ባዕታቸው ይዘውት ገቡ ።ከዛ ማንቆርቆሪያቸውን ጥደው ሻዩ እስኪፈላ መጠበቅ ጀመሩ ። ልጁም በሚገርም የወሬ ፍጥነት አባ ክርስትና እንዲ ነው አይደል ፡አባ ክርስትና እንደዛ ነው አይደል ?ሰዎች እኮ ነግረውኛል እያለ ከሰዎች የሰማውን ይቀባጥራል

መነኩሴውም ዝም ብለው ሲሰሙት ቆዩና ሻዩ ሲፈላ ብርጭቆ አምጥተው ይቀዱለት ጀመረ ። ብርጭቆው ሞልቶ እየፈሰሰም ዝም ብለው ይቀዳሉ ። ከዛ ልጁም አንተ መነኩሴ ያምሀል እንዴ ?ብርጭቆውኮ ሞልቷል ። አንተ ለምትጨምርበት ሻይ ቦታ የለውም አላቸው ። መነኩሴውም አየህ ልጄ አንተም እንደዚ ብርጭቆ ነህ ። ስለ ክርስትና ማወቅ ትፈልጋለህ ነገር ግን ልብህ ሌሎች በነገሩህ አሉባልታ ተሞልቷል እኔ የምነግርህን ነገር የምትቀበልበት ቦታ በልብህ ውስጥ የለም

ብነግርህም ታፈሰዋለህ ። ስለዚህ አሁን ሂድ ልብህ ባዶ ሲሆን ተመልሰህ ና ያኔ እነግርሃለው አሉት። እኛስ ዛሬ ልባችንን የሞላው ምንድነው ?ፍቅር ?ሰላም ?መቻቻል ?ታምኝነት ፣ ህብረት አንድነት ነው ወይስ አስቀድሞ ልባችን በተንኮል ፣ በሟርት ፣ በቅናት፣በሴሰኝነት ፣ በዘረኝነትና በጎጠኝነት ስለተሞላ ለመልካም ነገሮች ቦታ የለውም ?እስቲ እራሳችንን እንፈትሽ ልባችንን ሞልቶት እየፈሰሰ ያለው ምንድነው ?

@bisrategebrel
@bisrategebrel