2022-06-17 07:29:48
ቆንጆ ሁኑ!!!
አንተ ሰው ቆንጆና ያማርክ ለመሆን አስማት የሚመስሉ መንገዶችን ብነግርህስ?! ስትስቅ ቆንጆ ሁን፤ ስታኮርፍ ቆንጆ ሁን፤ ስትሰራ ቆንጆ ሁን። እስካሁን ቆንጆ ሳትሆን ያለፉ ጊዜያት ቢኖሩም፤ ከዛሬ ጀምሮ ቆንጆ ሆነህ መቀጠል ትችላለህ። ሳቂ፣ ዘና በዪ፤ ፊትሽን በፈገግታ ሙዪው። ዝም ብሎ ሳቅ ሳይሆን ደማቅና ሳቢ ይሁን። ዝም ብሎ ዘና ማለት ሳይሆን በስራ፤ በጉዞ፤ በትምህርትና በመሳሰሉት መስኮች ዘና ማለት። ከውስጥ ዘና ማለትሽ በፊትሽ፤ በአነጋገርሽና በተግባርሽ ስለምታወቅ ሁሉም ሰው ካንቺ ጋር መሆንን ይመርጣል። ሰው ሲፈልግሽ የሚሰማሽ ስሜት ራሱ የበለጠ ደስተኛ እንዲትሆኚ ያደርግሻል።
ሰው በየቀኑ የሚረብሹ፣ የማያናድዱ፣ የሚያስቀይሙና የተለያዩ አሉታዊ ስሜት እንዲሰማው ከሚያደርግ ነገር ጋር ሊውል ይችላል። እየተረበሸ፤ እየተናደደና እየተቀየመ ከዋለ ቆንጆ መሆኑ ይቀርበታል። መልከመልካም የሆኑ ሰዎች አሁን ባላችሁበት አካባቢ ይህን ባለማድረጋቸው ቁንጅናቸው ማንንም የማይስብ ሆኖ ታያላችሁ። ነገሮች ሲረብሹ እናንተ በተቃራኒው አትረበሹ። አትረብሸኝ አትበሉ፤ ራሳችሁ እንዳትረበሹ ማድረግ ነው በጣም የሚቀለው። ከሚረብሹ፤ ከሚያስቀይሙ ነገሮች የራሳችሁን ፊት በመንሳት ቆንጆና ተፈላጊነታችሁን ማግኘት ትችላላችሁ።
ከአለባበስ የበለጠ ውስጣችሁን ውድ፤ እንቁና የማይረበሽ አድርጉ። ዛሬ ላይ የምናነሳቸው ታላላቅ ሰዎች ነፍሳቸውን ውድ ስላደረጉ ነው የምንወዳቸው። ነፍስ እንዴት ውድ ልትሆን ትችላለች??? ምንም ማንገራገር አያስፈልግም። ነፍስ ውድ የምትሆነው በትዕግስት ብቻ ነው። በፍቅር ብቻ ነው። በስነምግባር ብቻ ነው። በመልካምነት ብቻ ነው። በትህትና በበጎ አሳቢነት ነፍሳችሁን ውድ ማድረግ ትችላላችሁ።
ስትሰሩ፤ ስትማሩም ቆንጆ ሁኑ። ከስራ ባልደረባ ጋር በፍቅር ስሩ። ከክፍል ጓደኞቻችሁ ጋር በፍቅር ተማሩ። ራሳችሁን እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ። ስትሳሳቱም ስህተታችሁን በማመን ራሳችሁን መግራት አለባችሁ። ስህተቱን የሚያምን፤ አምነው የሚያርም ሰው እጅግ በጣም ቆንጆ ነው።
እርግጠኛ ነኝ ማንም ሰው ቆንጆ መሆንን አይጠላም። ነገር ግን ሂደቱን መከተል፤ በትዕግስት መቆየት ይከብደዋል። ሁላችንም በዚህ ጉዳይ ራሳችንን ማየት አለብን። "በትዕግስት መወደድ እየቻልኩ፤ ለምን እጣደፋለሁ?" ብለን ራሳችንን እንጠይቅ።
አብራችሁ ስትሰሩ እና ስትማሩ ጓደኞቻችሁን አግዟቸው። በብዙ አትተቹ። በፍቅር ግን ግሰፁ። ከዚያ በኋላ ቆንጆ እንደሆናችሁ ስሜታችሁ ይናገራል። አየሩ፤ ንፋሱ፤ ፍጥረቱና መላው ዓለሙ ከእናንተ ጎን ይቆማል። የእናንተ ጓደኛና አፍቃሪ ዓለም ይሆናል። ሰው ሁላ "ከሱ ወይም ከሷ ጋር መዋል አለብኝ!" ማለት ይጀምራል። ቆንጆና ውብ ካልሆነ ሰው ማንም ተገዶ ካልሆነ ወዶ አብሮ ልሆን አይችልም። እኔም አላደርገውም። እናንተም አታደርጉም። ቆንጆ ሁኑ። አዎ ቆንጆ መሆን ይቻላል። ማንም ሰው ነፍሱ ከእርካሽ ነገሮች ከጠበቀ ቆንጆ ነው። ሙሉ አካል ሳይኖራቸው፤ ደህና ልብስ ሳይለብሱ የምንወዳቸው ሰዎች ነፍሳቸውን ውድ ስላደረጉ ነው። ቆንጆ ሁኑ። በአውቶቡስ እየሄዳችሁ፤ ለታላላቅ ሰው ቦታ ቢታሳዩና ተነስታችሁ ቢታስቀምጧችሁ፤ እዚያ በአውቶቡስ ውስጥ ያለ ሰው ሁሉም ደስ ይሰኛል። ዕድሉን ባያገኝ ዝም ይበል እንጂ አብሯችሁ መሆንን ይፈልጋል።
ቆንጆ ሁኑ። አሜን ቆንጆ ሆነን የምንውልበት ቀን እንዲሆን ፈጣሪ መልካም ፍቃዱ ይሁን።
@Fikrin_feligu
208 viewsTame, 04:29