Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅርን ስትፈልጉ .............. ሰዎች እኛ አብዛኛውን ጊዜ ለፍቅር ያለን አመለካከት እጅ | ❤ፍቅርን ፈልጉ❤

ፍቅርን ስትፈልጉ ..............

ሰዎች እኛ አብዛኛውን ጊዜ ለፍቅር ያለን አመለካከት እጅጉን ይደንቀኛል። ስለፍቅር ማወቅን እንፈልጋለን። "ከሱ የያዘኝ ፍቅር ነውን? ከሷስ የያዘኝ ፍቅር ነው አይደል?" እንላለን። ጾታዊ(የፍቅረኛ) ፍቅር ከምንም በላይ እሳታዊነት አለው። ያቃጥላል፤ ያንቀጠቅጣል፤ ያስቃል፤ ያስለቅሳል፤ ያስተክዛል፤ ያማል፤ ያሳዝናል፤ ያስደስታል፤ያስተቃቅፋል፤ ያስወስባል፤ በእርካታም ይመዘናል።

በህይወታችሁ ምንም ቢኖራችሁ እንኳን እንደ ጾታዊ(እንደፍቅረኛ) ፍቅር የሚያረካችሁ የለም። ፍቅረኛችሁን እንደማቀፍ፤ እንደመሳም፤ አብሮ እንደመዞር ያለ እርካታና ደስታ አታገኙም። የሚያረካችሁ ሁሉ የሚታፈቅሩት ነው። የማያረካችሁ የማታፈቅሩት ነው አላልኩም። በይበልጥ ግን የሚትረኩት በሚትረኩት ነው። ተደብቆ ለምን ሰዎች ከሚወዷቸው ሰዎች አብሮ የሚሆኑ ይመስላቸዋል? እኮ ለምን? ለምን ይደበቃሉ? የማያፈቅሩትና የማይፈቀሩ ከሆነ ይህን ሰዎች አዘውትሮ ያደርጉታል። ተለሙና ፍቅሬኛዬ ነበረች። አሁንም ዳግም አብረን ነን። እኛ አንደበቅም። እኛ አንዋሽም። እኛ ሳንጠጣ እንሰክራለን። እኛ ሳንበላ እናገሳለን። ለምን ቢባል እንፋቀራለን።

በዚህ አጋጣሚ ተለሙናን ላመሰግናት እወዳለሁ። ተለሙና ፍቅር ናት። እሷ እውነት ናት። እናም አፈቅራታለሁ። እሷስ? ልትሉ ይሆናል። ልክ ናችሁ። መጠይቃችሁ ትክክል ነው። እኔ ነኝ በፍቅሯ ቀድሜ ያበድኩላት። እሷም ተከተለች፤ አብረን አበድን። ፍቅር ሚዛን ነው። እንደሳብከው እሱም ይለጠጣል። ፍጹም አፍቃሪ ሁኑ፤ በፍጹም መፈቀር ከፈለጋችሁ። አብሮ አደግ ወዳችሁ፤ አፍቅራችሁ ፍቅር የተነፈጋችሁ በማፍቀራችሁ አትጸጸቱ። ተፈቃሪያችሁ ፍቅር ባይሰጣችሁ አትርገሙት። ተፈቃሪያችሁ ምን ጥፋት አለበት? እሱም እንደናንተው አፍቃሪስ ቢሆን? ፍቅር ይታገሳል። ፍቅር ይቅርታ ያደርጋል።

እኛ ይኼንን እያደረግን ፍቅር ሳናገኝ አንቀርም። ፍቅር ከንፈር መሳም ላይሆን ይችላል። ፍቅር መወሰብ ላይሆን ይችላል። ፍቅር መረዳዳት ላይሆንም ይችላል። እንደነዚያ ላይሆን ከቻለ ሌላም ነው ማለት ነው። ሌላ የማናውቀው የፍቅር ገጽታ አለ ማለት ነው። ፍቅር መታገስ ቢሆን እስከመች የመታገስ አቅም አለን? አላችሁ? ፍቅር ይቅርታ ማድረግ ቢሆን እናንተ እሰከመች ይቅር ትላላችሁ? አንድን ሰው አፍቅራችሁ ሳትከፉ፤ ሳትበሳጩ ከቆያችሁ በኋላ ምላሹንም ብትታገሱ ምን የሚደረግላችሁ ይመስላል? እስቲ ከፍ በሉና ለማሰብ ሞክሩ። ከፍ ብላችሁ ሲታስቡ ፍቅራችሁ ፍጹም ይሆናል። ዝቅ ካላችሁ ለሁሉም ነገር እምነትም ተስፋ የላችሁም። እምነትና ተስፋ የሌለው ደግሞ ፍቅርን ሊያገኝ አይችልም። ሲታፈቅሩ ከፍ ትላላችሁ። ሲታፈቅሩ ራሳችሁን ታውቃላችሁ ወይም አታውቁም። ፍቅርን ሲትፈልጉ አፍቅሩ። መፈቀር የሚፈልግ ያፍቅር። መልሱ መፈቀር እንዲሆንለት። ፍቅርን የሚፈልግ ሁልጊዜ ንጹህ ነው። መታጠብ አያስፈልገውም። ባይሆን ፍቅር የሌለው ቢታጠብ መልካም ይሆንለታል። ገላችንን ስንታጠብ በራስ መተማመናችንን እንደምጨምር ሁላ ራሳችንን በፍቅር ስናጥብ ሁሉ ነገራችን ይፀዳል።

@Fikrin_feligu