Get Mystery Box with random crypto!

........'ስምሽ ዴይ'......... ባህር ዳር ቆሜ በንፋስ ሽውታ ከጠለሉ በላይ በወጀብ ጋጋታ | ❤ፍቅርን ፈልጉ❤

........"ስምሽ ዴይ".........
ባህር ዳር ቆሜ በንፋስ ሽውታ
ከጠለሉ በላይ በወጀብ ጋጋታ
ምስልሽ ይታየኛል በግልጽ ገጽታ
በአብሮነት ጊዜያችን የነበረው ገላሽ
እፁብ ድንቅ ውበት ዛሬም አልተለየሽ

በትዝታ መረብ በውሃው መስታወት
ባይሆን ያገኘሁሽ በአካል በመበለት
ያቺ ቀን ያ.......................ቺ'ለት
ያንቺ ትሆን ነበር እንደግሪጎሪያኑ
"ስምሽ ዴይ" ተብሎ ስምንተኛ ቀኑ
ይህቺቱ ዓለም አንድ ቀን ጨምራ
"ስምሽ ዴይ" ብሎ ሁሉም ሲጠራ
በቀነ ቀመሩ አንቺ ስትወሺ
ይሆን ነበር ጊዜው ስምንተኛው ሺ

በትዝታ መረብ በውሃው መስታወት
ባይሆን ያገኘሁሽ በአካል በመበለት
ሀገር በሚያውክ በድምፅ ማጉያ
ስላንቺ መመለስ እሰብክ ነበር በአህዛብ መሰብሰቢያ

በትዝታ መረብ በውሃው መስታወት
ባይሆን ያገኘሁሽ በአካል በመበለት
ያለም መጨረሻ ዳግመ ምጻት
ይሆንልኝ ነበር የትንሳኤው ዕለት


@Fikrin_feligu