Get Mystery Box with random crypto!

ሰሞንኛ ጨዋታ (በእውቀቱ ስዩም) . . . ትናንት ቀለል ያለ ራት ለመብላት ፈለግሁ ፤ እናም” | Fikir Eske Mekabir

ሰሞንኛ ጨዋታ

(በእውቀቱ ስዩም)
.
.
.
ትናንት ቀለል ያለ ራት ለመብላት ፈለግሁ ፤ እናም” ባጫ ህንጻ “ ውስጥ
በሚገኘው የ” አማራ ባንክ” ቅርንጫፍ ጎራ ብየ በርከት ያሉ ሁለት መቶ ብሮችን
ሸመጠጥሁ፤ ምግብ ቤት ገብቼ ፥ ምግቡ አላግባብ ውድ ከሆነብኝ ሂሳብ
ለማካካስ ብዙ ነገሮች እጠቀማለሁ፤ ለምሳሌ ሬስት ሩም ገብቼ ለረጅም ጊዜ
እቆያለሁ፤ ባጭሩ ፥ሬስት ሩምን ርስት ሩም አደርገዋለሁ፤ ያን ቀን ወደ ቤተ-ሰገራ
ወሽንቤቱ ስራመድ መብራት ድርግምም አለ፤ ከግማሽ ሰአት የፈጀ ዘለግ ያለ
ሽንት ሸንቸ ሳበቃ እያፍዋጨሁ ስወጣ የጽዳት ሰራተኛዋ ፥

"ሴቶች ሽንት ቤት ውስጥ መሽናትህ የሚያሳፍር ነው “ አለችኝ ::
“ በዚህ ጨለማ ፥ ኪችን ውስጥ ባለመሽናቴ ልታደንቂኝ ይገባል “ ስላት ፈገግ
አለችልኝ ፤ (ግን ጨለማ ከሆነ ፈገግታዋ እንዴት ሊታየኝ ይችላል ? ሰው ምን
ይለኛል አይባልም? )
ባጭር ጊዜ የሌለ ተመቻቸን ፤መጨረሻ ላይ ቁጥርሽ ስንት ነው ?” ስላት፤ “
የጫማየ ወይስ የወገቤ” ብላ ስለመለሰችልኝ አጥብቆ ደበረኝ!
ድብርቴን ለማባረር የሚከተሉትን ሁለት ቀደዳዎች አስታወስኩ፥
ጉዋደኛየ ባለፈው ለአለቃው ‘ የሞተር መኪና አደጋ ስለደረሰብኝ ዛሬ መምጣት
አልችልም “ ብሎ ለአለቃው መልክት ሰደደለት፤ አለቅየው “ ይገርማል፤ ዛሬ
በጀት መዝጊያ ስለተቃረበ በመስርያ ቤታችን ውስጥ ሰርፕራይዝ ፓርቲ
አዘጋጅተን ነበር ፤ ለሰራተኞች ዳጎስ ያለ የገንዘብ ስጦታም አሰናድተናል፤
እንዲሁም ዳጎስ ዳጎስ ያለ መቀመጫ ያላቸው ሴቶች ፓርቲውን ያደምቁታል ፤
በዚህ ዝግጅት ተሳታፊ ባለመሆንህ የተሰማኝ ደስታ ማለቴ ሀዘን ወሰን የለውም
፤ ለማንኛውም ነፍስ ይማር፤ I mean እግዜር ይማርህ” ብሎ መለሰለት፤
ግብዣው በመጦፍ ላይ እያለ ረፍት የጠየቀው ጉዋደኛየ እንደቆሰለ አርበኛ
በሁለት ወንድሞቹ ግራናቀኝ ተደግፎ ከች አለ፤
አለቅየው እንዳየው ምን አለ ?
“ እያመመው መጣ! “
በዙ ጊዜ የሰይፉ ሾውን ስመለከት የራሴን ፈጠራ ነስነስ አደርግበታለሁ፤ ባለፈው
ሰይፉ የሀይሌ ገብረስላሴን ፊት ይዞ የተፈጠረ ሰውየ አቀረበ፤ ሰውየው ሀይሌን
እንዳገኘው “ ወንድሜ ! ብሎ እንደበረኛ ተጠመጠመበት ፥
ሀይሌ;- ወል እንግድ ! በአርባ ደቂቃ ውስጥ ለሚ ኩራ ደርሰህ ከተመለስህ
ወንድሜ መሆንህን እቀበላለሁ”
ሰውየው;- “ እሺ! አውቶቢስ ልያዝ ወይስ ራይድ ትጠሩልኛላችሁ? “
በመጨረሻ የዲኤን ኤ ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ መጣ
;
ሰውየው ;- በምርመራው መሰረት ወንድምህ መሆኔ ተረጋግጧል ፥ የሆነ ነገር
አታካፍለኝም?”
ሀይልሽ፤- ነገ ቢሮ ብቅ በልና የህይወት ልምዴን አካፍልሀለሁ”

Share


@fikireskemekabirtireka