Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር በዚያ ወራት (ሚካኤል.አ) #ክፍል 3 ከንፈሮቹን ልጎርሳቸው ተጠጋሁት.. ወደ ከናፍሩ ስጠጋ | Fikir Eske Mekabir

ፍቅር በዚያ ወራት
(ሚካኤል.አ)
#ክፍል 3
ከንፈሮቹን ልጎርሳቸው ተጠጋሁት.. ወደ ከናፍሩ ስጠጋ የውብ ትንፋሹ መዓዛ አወደኝ ። የተቀባው ሽቶ በአፉ ከሚያላምጠው ሜንት ማስቲካ ጋር ሲዳበል የገነት መግቢያው የሱ መዓዛ ነው ቢሉኝ ውሸት ነው አልልም።
ወድያው "አይዞሽ ውዴ! " የሚል ድምፅ ሰማሁ ።
ሺት !
የፈራኋት ጣውንቴ መጣች ። የነጃት ጥላቻዬ አስራ አንድ በመቶ ሲያድግ ተሰማኝ (ፖለቲካ አይደለም !)... በሷ ቤት አንድ ቀን ኒቃቧ ከፊቷ ሲወርድ ቀድሜ ስለደረስኩላት በችግሬ ጊዜ ቀድማኝ መድረሷ ነው። ችግሬ እሷ እንደሆነች ብታውቅ ስል ተመኘሁ።
"ነጅዬ እባክሽ handle " አድርጊያት ብሎ ዶክተር ወደ ክፍሉ ገባ። ነጅዬ ሲላት ደግሞ ነብር ሆንኩኝ... ከየት መጣ ያልተባለ ቀዝቃዛ ውሀ ፊቴ ላይ ከነበለችብኝ።
የዛክዬን ከናፍር ከመጉረስ ስታግደኝ ነው መቀዝቀዝ የጀመርኩት ።
"ተረጋጊ እንጅ ፀጉሬን ..." ብዬ ጮህኩባት ።
እሷ እንኳን ልትደነግጥ ወገቤ ስር ገብታ አነሳችኝ ። በጥፊ ጉንጯን ባቀላው ስሜቴ ነው ።
እሷና ጓደኞቿ አንከብክበው ጥላ ያላት አፀደ ስር አኖሩኝ ። ንፋሱ ከውሀው ቅዝቃዜ ጋር ተዳብሎ በረደኝ ።
ጥርሶቼ በእልህና ቅዝቃዜ ተንገራገጩ።
"አይዞሽ ንፁህ.. . "
ራስሽ አይዞሽ ብዬ ልመልስላት ይሆን?
አይኖቿ የሚስቁለት.. .ነፍሷ የምትፈነጥዝለት ዛኪን ልቀማት መሆኑን ማን ሹክ ባላት ?
...
ከዛ ክስተት በኋላ ወደ መደበቂያዬ ሮጥኩ !
ክለብ.. .
ጠጣሁ.. . አምሮቴ ንቅል እስኪልልኝ ጠጣሁ ።
ሞቅ እንዳለኝ ያየ አንድ ጎረምሳ የሚያጨሰውን ሺሻ ትቶ ወደኔ አቅጣጫ መጣ።
"ቆንጆ ነሽ" አለኝ።
ዝም!
"ምነው የከፋሽ ነገር አለ ?"
ዝም!
ምናለ ከዛኪ በስተቀር የዓለም ወንዶች ሁሉ ባያናግሩኝ? አባቴና ወንድሜ እንኳ እንዲያናግሩኝ የምፈልግ አይመስለኝም።
አሁን ይሄ የሰማይ ስባሪ የሚያህል ወደል እንዴት ያናግረኛል ?
ጠጪ ...አጫሽ ወንድ ነው ያስጠላኝ።
ያዘነ ለመምሰል ሞከረ !
ውሸት.. . አይኖቹ ውሸት! ...ሳቁ ውሸት...ንግግሩ ውሸት ...
ቆንጆ ነሽ ሲለኝ አመሰግናለሁ ቢለኝ ...አብረን እንፍታታ ብሎ ይቀጥላል ።
እሺ ብለው እኔ ጋር ለማስመሰል ውስኪ ያወርዳል።
ምድር ላይ ያፈቀራት ሴት እኔ ብቻ የሆንኩኝ ያህል አስመስሎ ይንከባከበኛል...ከዛ መተኛት !
አንዴ ጭኔ ስር ገብቶ በለሴን ከቀጠፈ እኮ በነጋታው ስልክ አያነሳልኝም።
ይሄ ህይወት ሰልችቶኛል.. . ነፍሴ ዛኪ ጉያ ገብታ መሸሸግ ትፈልጋለች ።
ሀጥያቴ የሚጠራው በሱ ላቦት ነው።
"ማሬ አመልሽም ?"
"ማርህን ጎዣም ፈልግ !" አንባረቅሁበት ። ከመቅፅበት ከስሬ በሮ ጠፋ ። ፈሪ ወንድ !
አሁን ይሄ ነው የኔን ጀንታላ ዛክ የሚተካልኝ?
ሌላ ብስጭት.. .
መጠጥ.. . ሻት ...
በቃ ራሴን አጣሁት ። የክለቡ ብልጭ ድርግም መብራት ...መጠጡ.. .ሙዚቃው ናላዬን አዞረኝ ።
ምንም ሆንኩ !
እንደምንም ተንገዳግጄ ሰው መሀል ገብቼ ጨፈርኩ።
እንደ ልማዴ የሰው ሆንኩ...ሳቄ ...ደስታዬ ሁሉ የሰው ሊሆኑ ራሳቸውን ከመቃብር ቀስቅሰው ተነሱ።
ከሩቅ ለሚያየኝ ሰው ደስተኛ ነኝ...ነፈዝኩ...ነጎድኩ ...ብንንንንንንንንንን....
አላልኩም ?
ስጠጣ የሰው ነኝ ብዬ አልነበረምን ?
ማልዶ ስነሳ ራሴን ከሰው ጋር አገኘሁት ።
አንሶላዬን ገልጬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ።
አብሮኝ ያደረው ወንድ እንደ ጆንያ ተንደባሎ ፊቱን ወደኔ አዞረ?
እንዴ?
ይሄ የኢኮኖሚክስ መምህሩ እዘዝ ነው እንዴ?
ዛኪ የነፍስና ገላዬን መርከስ አይቶ የጠላኝ መሰለኝ...
"አንተ ማነህ ?"
.
(ይቀጥላል)

@fikireskemekabirtireka