Get Mystery Box with random crypto!

ሀሌ ሉያ ለቤተክርስቲያን ሃነጻ ልዑል ለቤተክርስቲያን ሰኔ 21 ቀን ለመቅደሷ መቅደስ | ትምህርተ አበው

ሀሌ ሉያ ለቤተክርስቲያን
ሃነጻ ልዑል ለቤተክርስቲያን

ሰኔ 21 ቀን ለመቅደሷ መቅደስ የተሰራበት ዕለት ነው አማናዊት መቅደስ ድንግል ማርያም በስሟ መቅደስ በዛሬው ዕለት ታንጾላታል።በመቅደስ ጽላት እንደሚያድር አማናዊ ጽላት እግዚእነ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማህጸኗን ዓለም አድርጎ 9 ወር ከ5 ቀን የከተመባት አማናዊት መቅደስ ድንግል ማርያም ናት።

ይህች አማናዊት መቅደስ በታህሳስ 3 ስንክሳር እንደምናነበው የኖረችውም በሶሎሞን ቤተመቅደስ ነው የሚደንቅ ነው እርሷ ራሷ ቤተመቅደስ ኑሮዋ እና እድገቷም በቤተመቅደስ ዛሬ ደግሞ በስሟ ቤተመቅደስ ታንጾላታል።

በቤተክርስቲያን ሊቃውንት አስተምህሮ መሠረት ቤተመቅደስ ቤተመቅደስ ነው ለመባል ከሚያስፈልጉት መሰረታዊ ነገሮች አንዱ በውስጡ ታቦት መኖሩ ነው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ደግሞ "አንቲ ውእቱ ታቦት" ይላታል

ታቦት :-ማደርያ ማለት ነው በውስጡ ጽላት ይቀመጥበታልና በቀድሞው ጽላት ደግሞ በእግዚአብሔር ጣት 10ሩ ቃላት ተጽፈውበታል አምላካችን ክርስቶስ በማህፀኗ ያደረባት አማናዊት ታቦት ደግሞ ድንግል ማርያም ነች መቅደስ ያሏትን ታቦት ብለውም ያመሰጥሯታል ስለዚህ በአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ለመባል ድንግል ማርያም ልትኖርበት ያስፈልጋል።


ለዚህ ነው ሊቁ ስል እርሷ እንዲህ ያለው
"ዕበያ ለድንግል ኢይትከሃል ለተነግሮ (የድንግልንንና ገናናነትና ሊናገሩት አይቻልም)


ሰኔ 21/2014
ዲ/ን ፍቃዱ ጎንፋ (ዘፍቁረእግዚእ)
ከዮሐንስ ማርያም